“አልቶሰ ላብስ” ቤተ ሙከራ ህዋሶቻችን እድሜያቸውን የሚያድሱበት መንግድ ላይ እየሰራ ነው
አብዛኛው የሰው ልጅ ሞት ባይኖር እና ዘላለማዊ ቢሆን ፍላጎቱ ቢሆንም፤ ሞት የተፈጠሮ ህግ ነው እና ለማንም የማይቀር የተፈጠሮ ሂደት ነው።
“አልቶሰ ላብስ” ቤተ ሙከራ ግን የተፈጠሮ ኡደት የሆነውን “ሞትን ለማስቀረት ወጥኜ እየሰራሁ ነው” ማለቱ በርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።
በአሜሪካ እና በብሪታኒያ በጋራ የተመሰረተው የምርምር ኩባያው እርጅናን በማስቀረት ሞትን መከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ እየሰራ መሆኑም ነው በመገባደድ ላይ በሚገኘው የፈረንጆንቹ 2022 የተሰማው።
አልቶስ ስላብስ በስነ ህይወት ተሃድሶ (ባዮሊጂካል ሪፕሮግራሚንግ) ላይ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ አዲስ ይዞት የመጣው የምርምር ሀሳብ ደግሞ በሰዎች ህዋስ ላይ በመስራት እርጅናን ለማስቀረት ያለመ ነው።
አልቶስ ስላብስ ሀሳብም በስነ ህይወት ተሃድሶ (ባዮሊጂካ ሪፕሮግራሚንግ) ህዋሳቶቻችን እድሜያቸውን እንዲያድሱ ያደርጋል የተባለ ሲሆን፤ በዚህ መንገድም ሞትን ማስቀረት ይቻላል የሚል መላ ምትም ይዟል።
ቤት ሙከራው ሀሳቡን እውን ለማድረግም ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ተገለፀ ሲሆን፤ አዲሱ ኩባንያ ሳንዲያጎ፣ ካምብሪጅ፣ ብሪታኒያ እና ጃፓን ጨምሮ በርካታ ተቋማትን ማቋቋሙ ተሰምቷል።
አልቶስ ስላብስ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶችን በከፍተኛ ደሞዝ በመመልመል ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ተመራማሪዎች ህዋሶች (ሴሎች) እንዴት እንደሚያረጁ እና ያንን ሂደት እንዴት እንደሚቀይሩ ላይ ያልተገደበ ሳይንሳዊ ምርምር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ታዲያ ይህ የምርምር ሀሳብ የበርካታ ባለሀብቶችን ቀልብ መሳቡ የተገለፀ ሲሆን፤ አማዞኑ ስራ አስፈጻ ጄፍ ቦሴዝ እና ዩሪ ሚልነር ተጠቃሽ ናቸው።
አልቶስ ስላብስ ሞትን ማስቀረት ላይ እየሰራሁ ነው ማለቱን ተከትሎም ሞትን የማይፈልግ ብዙ ነውና የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት እንዳለቸገረውም ተነግሯል።
እውን ይሕ የምርምር ተቋ ሞትን ማሰቀረት ይችል ይሆን.? አብረን የምናየው ይሆናል