ልዩልዩ
ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሞት ተጋላጭነታው ከሌሎች ከፍ ያለ ነው- ጥናት
ወሲብ አለመፈጸም ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን የበለጠ እንደሚጎዳም ጥናቱ ጠቁሟል
የወሲብ ስሜት ማጣት ስለ ጤና ሁኔታ ፍንጭ ይሰጣልም ተብሏል
የጃፓኑ ያማጋታ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች ወሲብ እና ጤና ያላቸውን ዝምድና በሚመለከት ለዓመታት ሲያደርጉት የነበረውን ጥናት ይፋ አድርገዋል።
በጥናቱ ላይ እድሜያቸው 40 እና ከዛ በላይ የሆኑ 21 ሺህ ገደማ ስዎች የተሳተፉ ሲሆን በዚህ ጥናት መሰረትም ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ቶሎ የመሞት እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል።
እንዲሁም የሰዎች የወሲብ ፍላጎት ማጣት ስለጤናቸው ይናገራል የሚሉት እነዚህ ተመራማሪዎች አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የካንሰር ህመም፣ ስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ ክብደት መጨመር እና ጭንቀት የወሲብ ፍላጎትን ይገድላሉም ተብሏል።
በጥናቱ መሰረት የወሲብ ፍላጎት ማጣት በሴቶች በህይወት የመቆየት እድሜ ላይ ያለው ጉዳት አነስተኛ ነው።
በእድሜ የገፉ ወንዶች የወሲብ ፍላጎት ማጣት በሽታ የመከላከል አቅማቸውን በማዳከም ለተለያዩ ህመሞች እና በሽታዎች እንደሚያጋልጣቸው ተጠቁሟል።
እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ሰዎች ወሲብ የማይፈጹሙት ከማፈጽሙት ጋር ሲነጻጸሩ በሁለት እጥፍ የመሞት እድል አላቸውም ተብሏል።
ይሁንና ጥናቱ እነዚህ እድሜያቸው የገፉ ሰዎች በየስንት ጊዜው ወሲብ ቢፈጽሙ የተሻለ ነው ለሚለው መፍትሔ አላቀረበም።