ጎግል ኩባንያን የ2 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣልበት ያደረጉት ባልና ሚስቶች
ለ21 ዓመታት በቀጠለው ክርክር ጎግል ይህግ ጥሰት ፈጽሞ በመገኘቱ ለቅጣት ተዳርጓል
ጎግል ኩባንያ በአሜሪካ አውሮፓ እና ብሪታንያ በቀረቡበት ተመሳሳይ ክሶች ትፋተኛ ተብሏል
ጎግል ኩባንያን የ2 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣልበት ያደረጉት ባልና ሚስቶች
ሽቫን እና ባለቤቷ ራን ራፍበዜግነት የብሪታንያ ዜጎች ሲሆኑ ከ22 ዓመታት በፊት ነበር ፋንዴም የተሰኘ ዌብሳይት የከፈቱት፡፡
ባልና ሚስቱ ህን ዌብሳይት ያበለጸጉት በዓለም ላይ ያሉ ሸማቾች በበይነ መረብ አማካኝነት ግዢ ከመፈጸማቸው በፊት አገልግሎት ሰጪዎች የሚስከፍሉትን ዋጋ አማራጭ ዝርዝሮችን እንዲያገኙ የሚደርግ ነው፡፡
ሸማቾች በዚህ ዌብሳይት ላይ ተመሳሳይ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተቋማት የሚያስከፍሉትን ዋጋ በማየት እንደ ኪሳቸው እና ትራት ደረጃቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ ያስችላቸወዋል፡፡
ይሁንና ይህ ዌብሳይት ከጎግል ውጪ ባሉ የበይነ መረብ መፈለጊያ ድሮች ላይ ብዙ ተጠቃሚዎችን ሲያገኝ ከጎግል ላይ ግን በተጠቃሚዎች ድርቅ ሊመታ ችሏል፡፡
ሁኔታው ግራ ያጋባቸው እነዚህ ባልና ሚስቶች ጎግል ኩባንያን ለማግኘት እና ያጋጠመውን ችግር እንዲያስተካክል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ጎግል የመረጃ ፍለጋ ገበያውን በብቸኝነት በመቆጣጠር በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተባለ
ባልና ሚስቶቹም ጉዳዩን ይዘው ወደ ፍርድ ቤት ያመሩ ሲሆን በተደረገ ምርመራ ጎግል ሆን ብሎ ተወዳዳሪ ዌብሳይቶች እንዲከስሙ አልያም ተጠቃሚዎች ጋር እንዳይደርስ ሲያደርግ ተይዟል፡፡
ባልና ሚስቶቹ ጉዳዩን ይዘው ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸውን ተከትሎ ጎግል ከፋንዴም በተጨማሪ መሰል ድረገጾችን ሆን ብሎ ከማስታወቂያ የሚያገኘውን ገቢ ለመጨመር ሲል ሲጎዳ እንደቆየ ተረጋግጧል፡፡
ይህን ተከትሎም በአለማችን ቀዳሚው የመረጃ መፈለጊያ ድር የሆነው ጎግል በአውሮፓ፣አሜሪካ እና ብሪታንያ ከባድ ቅጣት ታልፎበታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኩባንያው ከ2017 ጀምሮ ፍርዱን ለማስቀየር በተለያዩ ሀገራ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ 2 ቢሊዮን ዩሮ ቅጣቱን ለመክፈል ተገዷል ተብሏል፡፡