የሀማስ ይዞታ የሆነችው ጋዛ ያለችበት ሁኔታ ምን ይመስላል?
የአረብ ሀገራት በጋዛ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቁም እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ አልተቀበሉትም
የሀማስ ታጣቂዎች ይጠቀሙበታል የተባለውን ውስብስብ የመሬት ውስጥ ዋሻ ማግኘት የዘመቻው ሁለተኛ ምዕራፍ ነው ተብሏል
የእስራኤል እግረኛ ጦር የጋዛ ከተማን ከከበበ ቀናትን አስቆጥሯል።
የጋዛ ከተማን የከበበው የእስራኤል እግረኛ ጦር የሀማስ ታጣቂዎች መሽገውበታል የተባለውን የመሬት ውስጥ ዋሻ ለማግኘት እና ታጣቂዎቹን ለመምታት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀማስ ታጣቂዎች ይጠቀሙበታል የተባለውን ውስብስብ የመሬት ውስጥ ዋሻ ፍለጋ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እንዲገደሉ ምክንያት የሆነው ዘመቻ ሁለተኛ ምዕራፍ ነው ተብሏል።
ሀማስ 1400 ሰዎችን ከገደለበት እና 240 ካገተበት የጥቅምቱ ጥቃት ወዲህ እስራኤል በጋዛ ያልተቋረጠ የአየር ድብደባ አድርጋለች፤ ጋዛን ከፋፍሎ ለማጥቃትም የእግረኛ ጦር አስገብታለች።
የሀማስ ዋና ይዞታ የሆነችው መሉ በመሉ ተከባለች። የእስራኤል ጦር በህዝብ ወደተጨናነቀችው የጋዛ ከተማ መሀል እየተጠጋ መሆኑን ሲገልጽ የሀማስ ታጣቂዎች ግን ወራሪ ባሏቸው የእስራል ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ይናገራሉ።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት እስራኤል "አንድ ኢላማ አላት፤ ይህም በጋዛ የሚገኘው የሀማስ አሸባሪ ነው።" ብለዋል።
ሚኒስትሩ እንደተናገሩት የሀማስ መሰረተልማት፣ አዛዦች፣ መደበቂያቸው እና የግንኙነት ቦታቸው የጥቃት ኢላማ ናቸው።
የጦር ዋና አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሀጋሪ የእስራኤል ጦር የምህንድስና ክፍል አባላት የሀማስን የመሬት ውስጥ ዋሻዎች ለማፈራረስ ፈንጅዎችን እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል።
የሀማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ታንኮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የእስራኤልን ጦር ግስጋሴ ለመግታት እየሞከሩ ነው ተብሏል።
የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት በጋዛ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ አስከትሏል።
የአረብ ሀገራት በጋዛ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቁም እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ አልተቀበሉትም።