የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት 60 ያህሉ ታጋቾች እንደጠፉበት በትናንትናው እለት አስታውቋል
ሀማስ ስለታጋቾቹ የለቀቀው አዲስ መረጃ የታጋቾችን ቤተሰቦች አስደንግጧል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ አንጃ ሀማስ ወታደራዊ ክንፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት ምክንያት 60 ያህሉ ታጋቾች እንደጠፉበት በትናንትናው እለት አስታውቋል።
የታጋቾቹ ቤተሰቦች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ እና ካቢኔያቸው ታጋቾቹ በሰላም የሚመለሱበትን መላ እንዲዘይዱ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
ቤተሰቦቹ ከተመጠየቅም አልፈው መንግስት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በቂ ጥረት አላደረገም በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ናቸው።
ሀማስ ባለፈው ወር ከታገቱት ውስጥ 50ዎቹ በጋዛ ውስጥ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን ገልጾ ነበር።
የአል ቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ኡባልዳ በቴሌግራም ገጹ በአየር ጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ የ23ቱ በፍርስራሽ ውስጥ መቀበራቸውን ተናግሯል።
"በጋዛ ላይ እየተካሄደ ባለው ከባድ እና ያልተቋረጠ ወረራ ምክንያት ልንደርሳላቸው የምንችል አይመስልም" ብሏል ቃል አቀባዩ።
ሮይተርስ ይህን ማረጋገጥ እንደማይችል እና በእስራኤል ጦር በኩልም ምላሽ እንዳልተሰጠው ጠቅሷል።
አሜሪካ ሀማስ እስራኤልን በጣቃበት ጊዜ የወሰዳቸውን ታጋቾች ለመፈለግ በጋዛ ሰማይ ላይ የቅኝት ድሮን ማብረሯን የአማሪካ ባለስልጣናት ባለፈው ሀሙስ መናገራቸው ይታወሳል።
ሀማስን እያስተዳደረ ያለው ሀማስ እስካሁን ከያዛቸው 239 ሰዎች ውስጥ አራት ታጋቾችን ለቋል።
ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት ያለመችው እስራኤል የጋዛ ከተማን በመክበብ ከዋሻ ውስጥ ወጥተው ጥቃት አድርሰው ከሚሸሹ የሀማስ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋች መሆኗን ገልጻለች።
እስራኤል ተኩስ እንድታቆም የቀረበላትን አለምአቀፍ ጥሪ ውድቅ አድርጋዋለች።