በጋዛ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአማካይ 6 ህጻናትና 5 ሴቶች ይሞታሉ
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት አንድ ወር አስቆጥሯል።
እስራኤልም በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ማድረጓን ቀጥላለች፤ ሃማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶቹን መተኮሱን ቀጥሏል።
አንድ ወር በደፈነው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ቁጥሮች ምን ይላሉ?
ሆስፒታሎች በየደቂቃው 1 የቆሰለ ሰው፤ በየሰዓቱ 15 አስከሬኖችን ይቀበላሉ።
6 ህጻናትና 5 ሴቶች በአማካይ በየአንድ ሰዓት ልዩነት ውስጥ ይሞታሉ።
70 በመቶ የጋዛ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ያለፍላጎታቸው በግድ ተፈናቅለዋል።
30 ሺህ ቶን ፈንጂ እስራኤል እስካሁን በጋዛ ላይ የጣለች ሲሆን፤ ይህም 82 ቶን ፈንጂ በ82 ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ ማለት ነው።
በጋዛ ግማሽ ያክል ሆስፒታል ወድመዋል፤ 62 በመቶ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ማእከላት ወድመዋል።
50 በመቶ መኖሪያ ቤቶች ጉዳት ድርሶባቸዋል፤ 10 በመቶ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
አንድ ሶስተኛ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ድርሶባቸዋል፤ 9 በመቶ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
14 በመቶ መስጊዶች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ከእነዚህም ውስጥ 5 በመቶ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሞትና ሰብዓዊ ቀውስ
በጋዛ
የሞቱ፤ 10022
ቆሰሉ፤ 25408
በዌስት ባንክ
የሞቱ፤ 163
የቆሰሉ፤ 2100
በእስራኤል
የሞቱ፤ 1405
የቆሰሉ፤ 5600