ኩላሊት እንደ ጎመን የሚሸጥባት የኔፓሏ ሆክስ መንደር
ደላሎች ደጋግመው የሚመላለሱባት ይህች መንደር በድህነት የሚኖሩ ወጣቶችን ኢላማ እንደሚያደርጉ ተገልጿል
ደላሎች ለወጣቶቹ ኩላሊታቸው ቢቆረጥም ዳግም እንደሚበቅል እና ምንም አይነት የጤና ጉዳት እንደሌለው ይነግሯቸዋልም ተብሏል
ኩላሊት እንደ ጎመን የሚሸጥባት የኔፓሏ ሆክስ መንደር
ኔፓል የተሰኘችው ሀገር በሕንድ እና ቻይና መካከል የምትገኝ እስያዊት ሀገር ስትሆን ወደብ አልባ ሀገር ናት፡፡
አብዛኞቹ የሀገሪቱ ዜጎች በድህነት እንደሚኖሩ የሚገለጽ ሲሆን ሆክስ በተሰኘችው መንደር ደግሞ ድህነቱ ከፍ ይላል፡፡
በእስያ የኩላሊት ንቅለ ህክምና የሚያደርጉ ሆስፒታሎች እና ደላሎች ትኩረታቸውን በዚች መንደር እንዳደረጉ ስካይ ኒውስ በምርመራ ዘገባው አረጋግጧል፡፡
በዚች መንደር ከሚኖሩ ወጣቶች አብዛኞቹ አንዱን ኩላሊታቸውን በትንንሽ ገንዘብ ሸጠዋል የተባለ ሲሆን በአማካኝ አንድ ኩላሊት 3 ሺህ ዩሮ በመሸጥ ላይ እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የጆሞ ኬንያታ ሆስፒታል ኩላሊታችንን ግዙን በሚሉ ሰዎች መማረሩን ገለጸ
ደላሎች እነዚህን በድህነት የሚኖሩ ወጣቶችን ኩላሊታቸውን ቢሸጡ መልሶ እንደሚበቅልላቸው፣ ምንም አይነት ጤና ጉዳት እንደማያመጣ እና በውድ ገንዘብ መሸጥ እንደሚችሉ እየነገሩ ያታልሏቸዋልም ተብሏል፡፡
እነዚህ ደላሎች ከዚች መንደር በርካሽ የሚያገኙትን ኩላሊት ወደ ሕንድ እና ሌሎች የእስያ ሀገራት በማጓጓዝ በውድ ዋጋ እንደሚሸጡ ተገልጿል፡፡
ደላሎቹ የኩላሊቱን ንቅለ ተከላ ለማድረግ አስቀድሞ በሚያደርጉት ምርመራ አማካኝነት በማዘጋጀት የኩላሊት ተከላው ለሚደረግለት ወይም ለሚደረግላት ሰው ወንድም ወይም እህት እንደሆኑ የሚስመስል ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ንቅለ ተከላውን ህጋዊ አስመስለው በሆስፒታል ውስጥ ያከናውናሉም ተብሏል፡፡
ኩላሊታቸውን ተታለው የሚሸጡ የኔፓል ወጣቶች ለተደራራቢ ህመም፣ መስራት አለመቻል፣ ለከፋ ድህነት እና ሌሎች ጉዳቶች እንደተዳረጉም ተገልጿል፡፡
በዓለም ላይ ከሚደረጉ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ህክምና ውስጥ አንዱ በህገ ወጥ መንገድ የተገዛ እንደሆነ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡