የወንዶች መካንነት ችግርን መከላከል የማይቻል ቢሆንም የዘር ፍሬ እንዳይቀንስ ግን ማድረግ ይቻላል ተብሏል
የወንድ የዘር ፍሬን ጤናማ ለማድረግ የሚጠቅሙ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
የአንድ ወንድ ሰው የዘር ፍሬ መጠን በአማካኝ ከ20 እስከ 150 ሚሊዮን እንደሚሆን ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ይህ ቁጥር በየጊዜው እየቀነሰ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ለወንድ የዘር ፍሬ መጠን መቀነስ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የሰው ልጆች በሚከተላቸው የህይወት ዘይቤ እና የአካባቢ አስተዋጽኦ ናቸው፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ፣ አመጋገብ እና ኬሚካሎች የወንድ የዘር ፍሬ መጠን መቀነስ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው የተባለ ሲሆን ሳይንስ አለርት የተሰኘው የጥናት ውጤቶች ማዕከል መፍትሔዎቹን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት የወንድ የዘር ፍሬ መጠን መቀነስን ለመከላከል አምስት ዋና ዋና መንገዶችን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡፡
የመጀመሪያው የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር መቻል ሲሆን ከልክ ያለፈ ውፍረት በወንድ የዘር ፍሬ ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ እንደሚቀንስ ተገልጿል፡፡
በወንድ የዘር ፍሬ ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ ሲቀንስ የዘር ፍሬ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ እና አነስተኛ ጥራት እንዲኖረው በማድረግ ቀስ በቀስ መሀንነትን ሊያስከትል ይችላል ተብሏል፡፡
የስብ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ምግቦች ማለትም እንደ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች ፣ የባህር ውስጥ ምግቦች እና ጥራጥሬዎች የወንድ የዘር ፍሬዎችን መጠን እና ጥራት እንደሚጨምሩም በጥናቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ሁለተኛው የወንድ የዘር ፍሬ መጠን እና ጥራትን የሚጎዱት አነቃቂ መድሃኒቶች ሲሆኑ እንደ ኮኬይን፣ ሄሮይን እና ተያያዥ መድሃኒቶች የወንድ የዘር ፍሬዎች መመረትን ይጎዳሉ ተብሏል፡፡
ለ550 ልጆች አባት የሆነው ሆላንዳዊ የዘር ፍሬውን እንዳይለግስ ታገደ
በሰውነት ውስጥ የተራጠቀመ ስብን ለማስወገድ የሚውሉ መድሃኒቶች ደግሞ የወንድ የዘር ፍሬ መጠንን ይጎዳሉ ተብለው ከተለዩት መንገዶች መካከል ሶስተኛው ነው፡፡
አራተኛው መንገድ ደግሞ ሲጋራ ማጨስ ሲሆን የትኛውንም አይነት ሲጋራ ማጨስ ሙሉ የሰው ልጅ ጤናን የሚጎዳ ቢሆንም መሀንነትን ከሚያመጡ መንገዶች መካከል ተጠቅሷል፡፡
አምስተኛው የወንድ የዘር ፍሬን የሚጎዳው ደግሞ ኬሚካሎች ሲሆኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች የምናውላቸውን ኬሚካሎች በምግብ እና አየር አማካኝነት ወደ ሰውነታችን ከገቡ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ሆርሞኖችን እንደሚጎዱ ተገልጿል፡፡