በ2014 ግማሽ ዓመት ከ3400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተደርገዋል-ዶ/ር ሹመቴ ግዛው
2014 ግማሽ ዓመት ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን ኢንሳ አስታወቀ
ባንኮች፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፤ የትምህርት ተቋማትና ሚዲያዎች የሳይበር ጥቃቱ ኢላማ ካደረጋቸው ተቋማት መካከል መሆናቸው ተገልጿል
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በግማሽ ዓመቱ ቢደርሱ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ከ3400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተሰንዝረው ነበር ብለዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ የተሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ከዚህ ቀደም በአንድ ዓመት ውስጥም ታይቶ አያውቅም ብለዋል።
ዶ/ር ሹመቴ እንደገለጹት ከፍተኛ ሙከራ የተደረገው እና 33 በመቶ የሚሸፍነው የሳይር ጥቃት ሙከራ ኢላማ ያደረገው በመሰረተ ልማት ቅኝት ላይ ነበር፡፡
- የግድቡን 2ኛ ዙር ሙሌት ለማደናቀፍ በ37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ ተነጣጥሮ የነበረ የሳይበር ጥቃት ማከሸፍ ተችሏል- ዶ/ር ሹመቴ ግዛው
- ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት መግለጫ በመሰረተ ልማቶች ቅኝት፣ በድረ-ገጽ፣ በሰርጎገብ፣በማልዌር፤መሰረተልማት ማቋረጥ እና ማህበራዊ ሚዲያን በመጥለፍ የጥቃት ሙከራች መደረገቸውን ገልጸዋል፡፡
የተሰነዘሩ የጥቃት አይነቶችም በቅደም ተከተል፡-
1 የመሰረተ ልማት ቅኝት 33 በመቶ
2 ድረ ገጽ 25 በመቶ
3 ሰርጎ ገብ (ባይፓስ) 21 በመቶ
4 ማልዌር 19 በመቶ
5 መሰረተ ልማት ማቋረጥ 10 በመቶ
6 ሶሻልሚዲያ ጠለፋ 8 በመቶ
7 ኦንላይን ማጭበርበር 2 በመቶ
በተሰነዘሩት ጥቃቶች ባንኮች፤አንሹራንስ ተቋማት፤ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋሞች፣ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፤ የትምህርት ተቋማትና ሚዲያዎች መሆናቸውን ዶ/ር ሹመቴ ገልጸዋል፡፡
የታላቁዉን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ በ37ሺ ኮምፒውተሮች ለይ ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር ኢንሳ ባለፈው ነሃሴ ወር መስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዶ/ር ሹመቴ ተነጣጥሮ የነበረውን የሳይበር ጥቃትን ቀድሞ ማከሸፍ መቻሉን መግጻቸው ይታወሳል፡፡