13,389, 955 ካሬ (1,338 ሄክታር) መሬትበህገወጥመንገድ በወረራ መያዙ ተገልጿል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመሬት ወረራና ባለቤት አልባ ህንፃዎች እንዲሁም በኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ለሁለት ወራት በባለሙያዎች በተካሔደ ጥናት እና የማጣራት ስራ ባዶ የሆነ የመንግስትን መሬት በወረራ በመያዝ ድርጊት በግለሰብ ደረጃና በኃይማኖት ተቋማትም ጭምር የተፈፀመ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል። የኮንደሚኒየም ቤቶችን በተመለከተም በህገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶች በጠቅላላው 21 ሺህ 695 ሲሆኑ ከ 10 ሺህ በላይ የቀበሌ ቤቶችም በህገወጥ መንገድ ተይዘዋል፡፡ 322 ባለቤት አልባ ቤቶችና ህንፃዎች መገኘታቸውንም ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡
4,076 በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ የንግድ ቤቶች መገኘታቸውንም ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡