“ታሪክ ፖለቲካን ሳይሸፍን፤ፖለቲካ ደግሞ ታሪክን ሳያደቅ” የየራሳቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው ምሁራን ይገልጻሉ
የታሪክ ምሁራንና ጸሀፊዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባት እንዲኖርና ታሪክ ፖለቲካን ሳይሸፍን፤ፖለቲካ ደግሞ ታሪክን ሳያደቅ የየራሳቸውን ሥራ ብቻ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡ እስካሁን በታሪክና በፖለቲካ መካከል ቅራኔ መኖሩንና ይህም ሊፈታ እንደሚገባ ነው ምሁራን በተደጋጋሚ ከሰጡት ሀሳብ መረዳት የሚቻለው፡፡