“የምናቅማማበት ጊዜ አይደለም” - የኮፕ28 ፕሬዝዳንት
ዶክተር ሱልጣን አልጀበር በሰጡት መግለጫ፥ ሀገራት ልዩነታቸውን አቀራርበው ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጠይቀዋል
በዱባይ ላለፉት 12 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በነገው እለት ይጠናቀቃል
በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ሀገራት የያዙትን አቋም አቀራርበው ከስምምነት ላይ ሊደርሱ እንደሚገባ የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን አልጀበር አሳሰቡ።
የጉባኤው ፕሬዝዳንት በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ “አሁን የማቅማማበት ጊዜ አይደለም፤ ጊዜ ሳናባክን ልዩነቶችን በማጥበብ ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርብናል” ብለዋል።
እንደ ድንጋይ ከሰል ባሉ ጉዳዮች ስምምነት ላይ በመድረስ የባለብዙ ወገን አለማቀፍ ስርአት እንደሚሰራ ለአለም ማሳየት አለብን ሲሉም ተደምጠዋል።
በዱባይ ላለፉት 12 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በነገው እለት ይጠናቀቃል።
ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4aiTP2C