እሰስካሁን 73,205 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 433 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል
እሰስካሁን 73,205 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 433 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል
እስከ ትናንት ግንቦት 14 ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 433 ሲሆን ከዚህም ዘግይቶ ሪፖርት የተደረገውን ጨምሮ 117ቱ ባለፉት 5 ቀናት የተገኙ ናቸው። በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ከ16 በመቶ በላይ የሚሆኑት የውጭ ጉዞና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው መሆኑ ደግሞ ዋነኛ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። እሰስካሁን የተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ 73,205 ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቫይረሱ የሚገኝባቸው አብዛኛው ሰዎች ከጎረቤት ሀገራት የሚገቡ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። ምንም እንኳን ድንበሮች ቢዘጉም ከመደበኛ የመውጫ እና የመግቢያ መንገዶች ውጭ የሚደረጉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች መቀጠላቸውን መንግስት አስታውቋል። ይህ ደግሞ ከኤርትራ ውጭ ሁሉም የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ በላይ የቫይረሱ ታማሚዎች እንደተገኙባቸው ሪፖርት ከማድረጋቸው አንጻር ሲታይ አሳሳቢነቱን ከፍ ያደርገዋል።
እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙ ኢትዮጵያዊያን መካከል ግማሹ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው። በአዲስ አበባ ደግሞ ልደታ ክፍለ ከተማ በተጠቂዎች ቁጥር ቀዳሚ ሲሆን መርካቶን የሚያካትተው አዲስ ከተማ ክፍል ከተማ ይከተላል።