ኮሮናን ለማከም የሚያስችል ሃገር በቀል መድኃኒት ተሰራ
ወደ ምርት እና ወደ ቀጣይ የእንስሳት እና ክሊኒካል ፍተሻዎች እንዲሸጋገር ስለመደረጉም ተገልጿል
የመድኃኒቱ የምርምር ሂደት ተጠናቋል የተባለ ሲሆን ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል
ኮሮናን ለማከም የተሰራው ሃገር በቀል መድኃኒት የምርምር ሂደቱ ተጠናቋል ተባለ
ሃገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት የኮሮና ቫይረስን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደቶችን ማለፉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ምርምሩ የቫይረሱ መከሰት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቅንጅት ሲካሄድ ነበር ያለው ሚኒስቴሩ ተደጋጋሚ የምርምር ሂደትን አልፎ ወደ ምርት እና ወደ ቀጣይ የእንስሳት እና ክሊኒካል ፍተሻዎች እንዲሸጋገር ስለመደረጉ አስታውቋል።
የምርምር ስራው በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣በጤና ሚኒስቴር፣በኢትዮጵያ የባህል ሃኪሞች እና የህክምና ተመራማሪዎች የሚካሄድ ሲሆን የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው።
አሁን ለተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የሚሆን መድሃኒት ባህላዊውን ከዘመናዊው ጋር አጣምሮ የመፈለጉ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተስፋ ሰጭ ሁኔታ እየታየ ነው ተብሏል።
መድሃኒቱ የመከላከል አቅምን የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፡፡
ወደ ምርት ለመግባት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡