በመላው አለም ከ10 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ
በአለማችን በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ውስጥ ሩቡ በአሜሪካ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳይሉ።
ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪውን ጠቅሶ ወርልድ ኦፍ ስታስቲክስ እንዳስነበበው፥ በአሜሪካ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች በእስር ቤቶች ውስጥ ናቸው።
አሃዙ የእስረኞቹ ቁጥር በፈረንጆቹ 1972 ከነበረበት በ10 እጥፍ መጨመሩን ያሳያል።
በአሜሪካ ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 629 ሰዎች በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።
ሲሸልስ፣ ሩዋንዳ እና ኤልሳቫዶርም ከጠቅላላ ህዝባቸው አንጻር በርካታ እስረኛ ያለባቸው ሀገራት ናቸው።
10 በርካታ ታራሚ የሚገኝባቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦