መጽሃፍ የሚያነቡ ታራሚዎችን በይቅርታ የሚለቀው የቦሊቪያ ማረሚያ ቤት
“የመጽሃፍት ገጾች ለይቅርታ” መርሃ ግብሩ ከ800 በላይ ታራሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል
ታራሚዎች ባነበቡት መጽፍት ብዛት ልክ የተፈረደባቸው የእስር ጊዜ ይቀነስላቸዋል
በተጨናነቁ የቦሊቪያ እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ታራሚዎች መጽሐፍትን በማንበብ የእስር ጊዜያቸውን መቀነስ እየቻሉ ነው ተባለ።
ከማረሚያ ቤቶቹ ውስጥ በተጀመረው አዲሱ “መጽሃፍት በእስር ቤቶች ውስጥ” በተባለ መርሃ ግብር ታራሚዎች ባነበቡት መጽፍት ብዛት ልክ የተፈረደባቸው የእስር ጊዜ እንደሚቀነስላቸው ተነግሯል።
መርሃ ግብሩ በአንድ ብራዚላዊ የተጀመረ ሲሆን፤ አላማውም የታራሚዎችን የማንበብ እና የመጽሃፍ ክህሎት ለማሳደግ እንደሆነ ሮይተርስ አስነብቧል።
መርሃ ግብሩ በሀገሪቱ በሚገኙ 47 ማረሚያ እና እስር ቤቶ የተጀመረ ሲሆን፤ የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ታራሚዎችም የትምህርትና ሌሎች የማህበራዊ ድጋፍ መርሃ ግብሮች ገንዘብ ለመክፈል አቅም የሌላቸው መሆናቸውንም የአንዲያን አካባቢ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ገልጿል።
መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ጊዜ እንስቶ እስካሁን 865 እስረኞች የማንበብ እና የመፃፍ ክህሎታቸውን ማሻሻል መቻላቸውም ተነግሯል።
የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ከሆኑ ታሳሪዎች ውስጥ ጃኩሊን አንዷ ስትሆን፤ በአንድ ዓመት ውስጥ 8 መጽፋት እንብባ መጨረሷን እና 4 የማንበብ ፈተናዎችን ማለፏን ትናገራለች።
“እንደኛ ላሉ ለትምህር ቤት ለመከፍለም ይሁን ከውጭ የሚደግፈን ቤተሰብ ለሌለን ሰዎች መርሃ ግብሩ በጣም ጠቃሚ ነው” ያለቸው ጃኩሊን፤ “እዝህ ያሉ በርካታ ሰዎች በመርሃ ግብሩ አማካኝነት ማንበብ እና መጻፍ እየቻሉ ነው” ብላለች።
አካባቢ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ሰራተኛዋ ናዲያ ክሩዝ፤ የመርሃ ግብሩ ዓላማ ፍርድ የሚጠባበቁ እስረኞችን ማበረታታት እንደሆነ አስታውቃለች።
በማንበባቸው ምክንያት ከተፈረደባው የሚቀነስላቸው የእስር ጊዜ እንደየ ወንጀላቸው ክብደት ከቀናት ጀምሮ ሊሆን ይችላል ያለች ሲሆን፤ አብዛኛው የእስር ጊዜ የሚቀነሰው በይቅርታ ቦርድ ውሳኔ መሰረት ነው ብላለች።