ከፍተኛ እስረኛ ያለባቸው የአውሮፓ ሀገራት
በአውሮፓ ያሉ እስረኞች ብዛት ወደ 475 ሺህ ከፍ ብሏል ተብሏል
ሀንጋሪ፣ ፖላንድ እና ፈረንሳይ ብዙ እስረኞች ያሏቸው ሀገራት ናቸው
በአውሮፓ ከሚወለደው ሰው ይልቅ ወደ እስር ቤት የሚገቡ ዜጎች ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ።
ዩሮ ኒውስ የአውሮፓ ስታትስቲክስ ማዕከልን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ በአውሮፓ ባለፉት ዓመታት ወደ እስር ቤት የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
ሀንጋሪ፣ ፖላንድ እና ፈረንሳይ በአንጻራዊነት ብዙ እስረኞች ያሏቸው የአውሮፓ ሀገራት ናቸው።
ፊንላንድ፣ ስሎቬንያ እና ሆላንድ ደግሞ ጥቂት እስረኞች ያለባቸው ሀገራት እንደሆኑ ተገልጿል።