በህንድ አስካሁን 14 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል
ህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አስታወቀች።
በሀገሪቱ በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ ለ7 ቀናት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።
ይህንን ተከትሎም በሀገሪቱ የሆስፒታል አልጋዎች እንዲሁም የመተንፈሻ ኦክሲጅን አቅርቦት ላይ እጥረት ማጋጠሙን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በዛሬው እለት ባወጣው መረጃ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ 200 ሺህ 739 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን አስታውቋል።
በ24 ሰዓቱ የ1 ሺህ 38 ሰዎች ህይወትም በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን ፣ እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 173 ሺህ 123 መድረሱም ተነግሯል።
በህንድ አስካሁን 14 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡ ይህም በዓለም ቦኮሮና ቫይረስ በብዛት በተያዙ ሰዎች ቁጥር ህንድን ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።