ሕንድ የሀገራት የካርበን ልቀት መጠን በህዝብ ብዛት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ጠየቀች
አሜሪካ፣ ሩሲያ እና የአውሮፓ ህብረት የዓለማችን በካይ ጋዝ ለቃቂ ሀገራት ናቸው
ሕንድ የአውሮፓ ህብረትን በመተካት ሶስተኛዋ በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ ላኪ ሀገር ተብላለች
ሕንድ የሀገራት የካርበን ልቀት መጠን በህዝብ ብዛት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ጠየቀች።
ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ሙቀት በማስተናገድ ላይ ስትሆን ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ ነው ተብሏል።
ሀገራት ለፋብሪካዎቻቸው ምርት በሚል በሚጠቀሙት ሀይል ምክንያት ወደ ከባቢ አየር የሚላከው ካርበን መጠን እየጨመረ እንደሆነም ተገልጿል።
በፈረንጆቹ 2020 ላይ ይፋ በተደረገው የሀገራት በካይ ጋዝ መጠን ሪፖርት መሰረት ቻይና፣ አሜሪካ እና ሕንድ ዋነኛ በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር የሚልኩ ሀገራት ተብለዋል።
ሕንድ ይህን ደረጃ የተቃወመች ሲሆን ደረጃው በህዝብ ብዛት ሊሆን ይገባል ስትል ገልጻለች።
ሕንድ ሪፖርቱን የተቃወመችው የአውሮፓ ህብረት በካይ ጋዝ መጠንን ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ አውሮፓ ህብረት ያነሰ አፈጻጸም አለው መባሉን ተከትሎ ነው።
ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ ወደ ከባቢ አየር የተለቀቀ የካርበን መጠንን የቀነሱ ሀገራት የካርበን ክፍያ በማግኘት ላይ ናቸው።
ሕንድ ሪፖርቱን የተቃወመችው የአውሮፓ ህብረት ከሕንድ ህዝብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው፣ ሪፖርቱም የህዝብ ብዛትን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል ብላለች።
በዓለም አየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው የኮፕ28 ጉባኤ የፊታችን ሕዳር በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ይካሄዳል።