አረብ ኢምሬትስ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ የመሪነቱን ሚና እየተወጣች ነው- አምባሳደር ፋሮክ
ቱርክ የኮፕ29 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ማዘጋጀት እንደምትፈልግ ገለጸች
የኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከአራት ወራት በኋላ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ይካሄዳል
አረብ ኢምሬትስ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ የመሪነቱን ሚና እየተወጣች መሆኑን በአውሮፓ ህብረት የቱርክ አምባሳደር ፋሩክ ካይማክጂ ገለጹ።
አምባሳደር ፋሩክ ካይማክጂ ለአል ዐይን ኒውስ እንዳሉት አንካራ ኮፕ29 ዓለም አቀፍ ጉባኤን የማዘጋጀት ፍላጎት አላት።
የኮፕ28 ዓከም አቀፍ ጉባኤን የምታዘጋጀው የተባበሩት አረብ ኢምሬት የአየር ንብረት አጀንዳ መሪ ሀገር መሆኗንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
እንደ አምባሳደር ፋሩክ ገለጻ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰባትን ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ የመሪነቱን ሚና እየተወጣች መሆኗንም አምባሳደር ፋሮክ ገልጸዋል።
በአውሮፓ መዲና ብራስልስ በተካሄደ የሚንስትሮች ጉባኤ ላይ የተሳተፉት አምባሳደር ፋሮክ እንዳሉት የተባበሩት አረብ ኢምሬት የአረብ ሀገራትን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሀገራት ወደ ትብብር እና ወደ ተግባር እንዲገባ በናድረግ ላይ ነች ብለዋል።
የኮፕ29 የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት እስካሁን ፍላጎታቸውን የገለጹ ሀገራት የሌሉ ሲሆን ቱርክ የማዘጋጀት ፍልጎት እንደምትፈልግ በቅርቡ ለተመድ እንደምታቀርብ ገልጻለች።
ደቡብ አሜሪካዊቷ ብራዚል ኮፕ30 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤን የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ አስታውቀዋል።