"ሜድ ኮፕ አየር ንብረት" ለኮፕ 28 መንገድ የሚከፍተው ጉባዔ
ከ1 ሺህ 500 በላይ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች የሚሳተፉበት ጉባኤው በሞሮኮ ይካዳል
"ሜድ ኮፕ የአየር ንብረት ጉባኤ" ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖ ለመቋቋም አዲስ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል
ከከንድ ሽህ 500 በላይ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች የተሳተፉበት በሞሮኮ የሚካሄደው "ሜድ ኮፕ የአየር ንብረት ጉባኤ" ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖ ለመቋቋም አዲስ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።
የታንጀርስ ከተማ (ሰሜን ሞሮኮ) ለሁለት ቀናት የሜዲትራኒያን የአየር ንብረት ፎረም የአየር ንብረት ጉዳዮች ላይ ያተኮረው "ሜድ ኮፕ አየር ንብረት" የተሰኘውን ሦስተኛውን ክፍለ ጊዜ አስተናግዳለች።
በጉባኤው ከአንድ ሽህ 500 በላይ የሞሮኮና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች እና የአየር ንብረት ጉዳይ ተመራማሪዎች እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናት፣ የግሉ ዘርፍ እና የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ተሳታፊዎቹ እንደ "ዘላቂ የምግብ ሥርዓት"፣ "የአየር ንብረት ለውጥን የሚለምዱ ከተሞችና ክልሎች"፣ “ዘላቂ የውኃ ኃብት አስተዳደር እና ሰማያዊ ኢኮኖሚ"፣ "የኃይል ሽግግር"፣ "ሴቶችና የአየር ንብረት"፣ "የአየር ንብረት ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረግ" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
"በተፈጥሮ ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎች"፣ "የአየር ንብረት ስደት"፣ እና "ሰላም፣ ደህንነት እና ያልተማከለ ትብብር" የሚሉ ጉዳዮችም ተነስተዋል።
የ "ሜድ ኮፕ" ጉባኤ ተሳታፊዎች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖን ለመቋቋም አዳዲስና ተጨማሪ ገንዘቦችን እንዲያቀርቡ፣ እንዲላመዱ እና ችግሩን እንዲከላከሉ ጠይቀዋል።
ተሳታፊዎቹ በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ስምምነት ማዕቀፍ በተጨማሪ ገንዘብ እንዲቀርቦ አሳስበዋል።