የግሉ ዘርፍ ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስን ማቅረብ ይችላል- ሱልጣን አል-ጃብር
የአየር ንብረት ፋይናንስን በበቂ፣ ቀላል እና ምክንያታዊ ወጪ ለማቅረብ አስፈላጊ በሆኑ ዘዴዎች ላይ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ጉባኤ (ኮፕ 28) በሚቀጥለው ህዳር በዱባይ ይካሄዳል
በፓሪስ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር ከቃል ወደ ተግባር እና ስኬት መሸጋገር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
አል ጃብር ይህን ያሉት በፓሪስ የግል ካፒታልን ለመሳብ በተዘጋጀው ከፍተኛ የፓናል ውይይት ላይ ነው።
የአየር ንብረት ፋይናንስን በበቂ፣ ቀላል እና ምክንያታዊ ወጪ ለማቅረብ አስፈላጊ በሆኑ ዘዴዎች ላይ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የኮፕ 28 ጉባኤ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚካሄድ ሲሆን፤ ጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በመገምገም የፓሪሱን ስምምነት ግቦች እንደሚለኩ ይጠበቃል።
- ኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ለአፍሪካዊያን የተለየ ጥቅም እንደሚያመጣ ተገለጸ
- የኮፕ 28ን ስኬት ለማረጋገጥ 'የነባር ህዝቦች' አስተዋጾ ወሳኝ ነው- ሱልጣን አል ጃበር
ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል-ጀበር አክለውም "የግሉ ዘርፍ ካፒታል ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስን ለማቅረብ የሚፈለግ መሰረታዊ እድገት ነው" ሲሉ በበቂ ሁኔታ ለአየር ንብረት ኢንቨስትመንት መሳብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል-ጀብር "የአየር ንብረት ፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸ፣ ማፋጠን ተከታታይ እና ወጥ ደረጃዎችን በአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና በልዩ ፈንድ መተግበር የበለጠ ፍትሃዊ መንገድን ለመተግበር እንደሚያስፈልግ" ጠቅሰዋል።
በ2015ቱ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት እና በ2030 የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ግቦች መካከል ባለው ወሳኝ ወቅት ኮፕ 28 ይመጣል።
እናም ግቦችን በመተግበር ረገድ መሻሻልን ለመገምገም ከመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ስሌት ጋር በመገጣጠም ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ለመፈተሽ ጠቃሚ እድል ይሰጣል።