ህንድ የቡድን20 ጉባዔን ለመጠበቅ 130ሺ የጸጥታ አስከባሪዎችን ማሰማራቷን ገለጸች
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን እንደማይሳተፉ እና በምትካቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እንደሚልኩ ተገልጿል
የዓለም ኃያል ሀገራት መሪዎች የሚገኙበትን ጉባዔ ማስተናገድ መቻል የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን እና ሀገሪቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተጽዕኖ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል ተብሏል
ህንድ በዚህ ወር የምታዘጋጀውን የቡድን20 አባል ሀገራት ስብሰባ ደህንነት ለመጠበቅ 130ሺ የጸጥታ አስከባሪዎችን ማሰማራቷ ገልጻለች።
የዓለም ኃያል ሀገራት መሪዎች የሚገኙበትን ጉባዔ ማስተናገድ መቻል የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን እና ሀገሪቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተጽዕኖ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል ተብሏል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እስከ ሳኡዲ አረቢያ ፕሬዝደንት ሞዛመድ ቢን ሳልማን የመሳሰሉ ህንድ ከዚህ ቀደም አስተናግዳቸው የማታውቃቸው ትላልቅ እንግዶችን ትቀበላለች።
የቻይናው ፕሬዝደንት ዥ ጅንፒንግ በጉባዔው እንደማይሳተፉ የቤጅንግን እና የኒው ዴልሂን ምንጮች ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
በዚህ ጉባዔ የጃፖን፣ የጀርመን እና የፈረንሳይ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገርግን በዩክሬን እያካሄዱት ባለው ጦርነት ከምዕራባውያን ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸው ያሉት የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን እንደማይሳተፉ እና በምትካቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን እንደሚልኩ ተገልጿል።
የተመድ፣ የአለም ባንክ፣የአለም ንግድ ድርጅት እና የአለም ጤና ድርጅት ኃላፊዎች በጉባዔው ይሳተፋሉ ተብሏል።
ጉባዔው የሚካሄደው በዓለም ብዙ ቀጥር ያለው ህዝብ ባለባት ከተማ መሀል በሚገኘው እና እድሳት በተደረገለት በድፔንድራ ፖታክ የስብሰባና እና የኢግዚቢሽን ማዕከል ነው።
ጉባዔውን ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ ሰልፎቾ እንዳይኖሩ ለማድረግ ተጠባባቂ የድንበር ጠባቂዎችን ጭምር ያሳተፈ የጸጥታ ማስከበር ስራ እንደማሰራ የኒው ዴልሂ ፖሊስ ገልጿል።