የቻይናውያን ጎብኝዎች ቁጥር በ60 በመቶ ቀንሷል
የህንድ ቱሪስቶች ወደ ደቡብ ምሥራቅ እስያ እየጎረፉ ሲሆን፤ የዓለምን በህዝብ ብዛት የተቆጣጠረችው ሀገር ለጉዞ እና የቱሪዝም ዘርፍ ቁልፍ ገበያ እየሆነች ነው።
ይህም ከቻይና ይገኝ የነበረውን ገቢ የሚያካክስ ነው ተብሏል። በኮሮና ወረርሽኝ ተመትቶ የነበረው የቻይና የቱሪዝም ዘርፍ የማንሰራራቱ ሂደት በጣም ዘገምተኛ ነው።
እንደ ኢንዲጎ እና ታይ ኤርዌይስ ካሉ አየር መንገዶች ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ክፍሎችን የሚያቀርቡ የመስተንግዶ ኩባንያዎች፤ በህንድ እያደገ ከመጣው የወጪ ኃይል እየተቋደሱ ነው ሲሉ ተንታኞች ተናግረዋል።
የአቪዬሽን ተንታኝ ብሬንዳን ሶቢ እንደተናገሩት "ደቡብ ምስራቅ እስያ ከህንድ ሊመጡ ለሚችሉት በርካታ የእድገት ምንጮች በጣም ጥሩ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው"።
የጉዞ እና የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለበርካታ የደቡብ ምስራቅ እስያ ኢኮኖሚዎች ወሳኝ ሲሆን፤ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት 12 በመቶ የሚሆነውን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አስተዋጽዖ አድርጓል።
ከ40 ሚሊዮን በላይ የክልሉን ህዝብ ቀጥሮ እንደሚያሰራም የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት አስታውቋል።
ለአስር ዓመታት ያህል ዘርፉ በቻይና ሲንቀሳሳ ቆይቷል። ነገር ግን ከአራት ደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት የተገኘው ይፋዊ መረጃ፤ የቻይና ከወረርሽኙ ማገገም ደካማ እንደሆነ ያሳያል።
በግንቦት ወር የቻይናውያን ጎብኝዎች ቁጥር በ2019 ከተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ቢያንስ በ60 በመቶ ያነሰ ነው።
በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ህንድ አዲሷ ቻይና ሆና ልትወጣ ትችላለች ተብሏል።