የሁለቱ ሀገራት የንግድ መጠን ከ84 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል
ህንድና አረብ ኤምሬት የሩፒ-ድርሃም ክፍያ ዘዴን ሊጀምሩ መሆኑን ገለጹ።
የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዋና ከተማ አቡ ዳቢ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊድ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለመምከር ነው አቡ ዳቢ የገቡት።
ከጉብኝቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመንግስት ምንጮች እንዳሉት ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሁለትዮሽ የንግድ ትስስር የሩፒ-ዲርሃም ክፍያ ዘዴ መጀመርን ሊያበስሩ ይችላሉ።
ህንድ የክፍያ ዘዴውን በመጠቀም ዘይት እና ሌሎችን ምርቶች ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ትሸምታለች ተብሏል።
አቡ ዳቢ ለህንድ አራተኛዋ ትልቅ ዘይት አቅራቢ ሀገር ናት።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ሦስተኛ ትልቅ የነዳጅ ዘይት ሸማች የሆነችው ህንድ፤ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዶላር ትከፍላለች።
ባለፈው ዓመት ማዕከላዊ ባንኳ የአለም ንግድን በሩፒ ለማረጋጋት የሚያስችል ማዕቀፍ አስተዋውቋል።
በህንድ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለው የሁለትዮሽ ንግድ እ.አ.አ በ2022/23፤ 84 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።