ሰራተኞች ከቢሮ እንዳይወጡ እንዲቆለፍባቸው ያደረገው የህንድ ኩባንያ አነጋጋሪ ሆኗል
የመስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ያለእሱ ፍቃድ ሰራተኞች እንዳይወጡ በሚል ህንጻውን አስቆልፎታል
የኩባንያው ስራ የሰራተኖች ብዝበዛና የስራ አካባቢን የሚጎዳ ነው በሚል ቁጣ ቀስቅሷል
በህንድ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሰራተኞቹ በስራ መሃል ከቢሮ እንዳይወጡ ለመከልከል ህንጻውን ይቆልፍባቸው ነበር መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል።
የመስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ያለእሱ ፍቃድ ሰራተኞች እንዳይወጡ በሚል ህንጻውን ያስቆልፍባቸው እንደነበረም ነው የተገለጸው።
በህንድ ጉሩግራም የሚገኝ ኒንጃስ ኮዲንግ የቴክኖሎጂ ኩባያ የጥበቃ ሰራተኛ የህንጻውን በር በትልቅ ሰንሰልት ና በትልቅ ቁልፍ በማድረግ ሲቆልፈው የሚያሳይ ቪዲዮ በማባረዊ ትስስር ገጾች ላይ ሲዘዋወር ቆይቷል።
ጥበቃው ሰራተኛው በሩን የቆለፈው በኩባያው ስራ አስኪያጅ ታዞ መሆኑን እና ያለ ስራ አስኪያጁ ፈቃድ ማንም ሰው ከህንጻው እንዳይወጣ በመታዘዙ እንደሆነም ተናግሯል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቀው ቪዲዮም የሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛ እና የስራ ቦታ ተነሳሽነትን የሚጎዳ ነው በሚል ቁጣን መቀስቀሱንም ኦዲቲ ሴንተራል አስነብቧለረ።
ኩባንያው በቅርቡ ክስተቱን አምኖ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ “መረጃው ደበረሰን በደቂቃዎች ውስጥ ማስተካከያ ተደርጓሲ ስልም አስታውቋል።
የኮዲንግ ኒንጃስ ኩባያ ቃል አቀባይ “የተፈጠረው ክስተት በኮዲንግ ኒንጃስ እንደ ድርጅት እሴቶቻችንን እና ባህላችንን የሚጻረር ነበር” ብለዋል።
“በክስተቱ እና በፈጠረው ችግር እናዝናለን” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “ይህ እርምጃ ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ለሁሉም ማረጋገጥ እንፈልጋለን” ሲሉም አስታውቀዋል።