በኢንዶኔዥያ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በተፈጠረ ግርግር ከ120 በላይ ሰዎች መቱ
አሬማ ኤፊ እና ፔርስባያ ሱራባያ የእግር ኳስ ክለቦቸ መካከል በተደረገ ጨዋታ ላይ ነው ግርግሩ የተፈጠረው
በምስራቅ ጃካርታ የሚገኙ ደጋፊዎች ክለባቸው መሸነፉን ተከትሎ አመጽ አንስነስተዋል
በኢንዶኔዢያ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የተፈጠረ ግርግርን ተከትሎ ከ120 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።
በምስራቅ ጃካርታ በአሬማ ኤፊ እና ፔርስባያ ሱራባያ መካከል በተደረገ ጨዋታ ላይ በተፈጠ ግርግር የሰዎች ህይወት ማለፉን ሮይተረስ ዘግቧል።
የተፈጠረውን ግርግር ተከትሎም በተፈጠረ መገፋፋት እና መረጋገጥ የ5 ዓመታ ህጻን ልጅን ጨመሮ 129 ሰዎች ሲሞቱ ከ180 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ግርግሩ የተፈጠረው በሜዳው የሚጫወተው ክለብ መሸነፉን ተከትሎ የተበሳጩ ደጋፊዎች ወደ ሜደ ዘላው በመግባታቸው ነው።
ግርግሩን ለመቆጣጠርም በስፍራው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን፤ ይህንን በመሸሽ ላይ በነበሩ ደጋዎች ላይ መረጋገጥ እና መተፋፈን መፈጠሩን የመስራቅ ጃካርታ ፖሊስ አዛዥ አስታውቀዋል።
የኢንዶኔዢያ የመገናኛ ብዙሃን በለቀቁት ምሰል በአሬማ ኤፊ እና ፔርስባያ ሱራባያ የእግር ኳስ ክለቦች መካከል መካከል በተደረገ ጨዋታ ላይ መሆኑን የፀጥታ አካላት አስለቃሽ ጭሶችን ወደ ሰማይ ሲቱክሱ ያሳያል።
የዓለም አቀፉ የአግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በፀጥታ አካላት በእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወይም " አስለቃሽ ጋዝ" መጠቀም እንዳልነበረባቸው ገልጿል።