በአርጀንቲና በእግር ኳስ ሜዳ በተፈጠረ ረብሻ አሰልጣኝ በጥይት ተመቱ
አሰልጣኙ ወደ ሆስፒታል ተወስደው አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉም ነው የተባለው
በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል
በአርጀንቲና የሶስተኛ ዲቪዥን ክሎቦቹ ሁራካን ላስ ሄራስ እና ፌሮ ካረል ኦስቴ ሲያደርጉት በነበረ የእግር ኳስ ግጥሚያ መሃል ባገጠመ ረብሻ የክለብ አስልጣኝ በጥይት መመታታቸውን ተገለጸ፡፡
በአርጅንቲናዋ ሜንዶዛ ግዛት በሁለቱም ክለቦች ሲካሄድ በነበረው የእግር ኳስ ግጥሚያ ፤ የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች ተኩስ ልውውጥ ሲደርጉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚድያ እየተንሸራሸረም ይገኛል፡፡
በሜዳ የተፈጠረውን ረብሻ ተከትሎ የሁለቱም ክለቦች ተጫዋቾች ሜዳ ለቀው እንደሸሹም ሚረር/MIRROR/ ዘግቧል፡፡
በተኩስ ልውውጡ መኃልም የፌሮ ካረል ኦስቴ አስልጣኙ ማውሪስዮ ሮመሮ ተከሻቸው አካባቢ በጥይት ሊመቱ ችሏል፡፡አሰልጣኙ በጥይት መመታታቸው ተከትሎም በስታድየሙ ውስጥ የመጀመርያ እርዳታ ካገኙ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል፡፡
የክለቡ አስተዳዳር “አሰልጣኙ አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ ለከፋ አደጋ የሚያጋጥም ጉዳት አላጋጠማቸውም” ብሏል፡፡
ጨዋታው ተቋረጠው በሁለተኛው ግማሽ ሲሆን ሁራካን ፌሮን 3 ለ1 ሲመራ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝመዋልም ነው የተባለው፡፡ሁረካን ላስ ሀራስ ክለብ በረብሻው የታሳተፉትን የክለቡ ደጋፊዎች አውግዟል፡፡
ክለቡ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት"እውነተኛ ደጋፊዎቻችን በረብሻ ምክንያት ከሜዳ ርቀው ቆይቷል፤ ክለባችንን የሚያዳክሙትን አርቆ ቀንደኛ ደጋፊዎቻችን እንዲያመጣልን ምኞታችን ነው"ብሏል፡፡