መነፅሩን በቀን ከ60 እስከ 90 ደቂቃ ማድረግ የሩቅ እይታ ችግርን ለመቅረፍ በቂ ነው ተብሏል
የሩቅ እይታ ችግርን የማከም አቅም እንዳለው የተነገረለት “ኮቡታ መነፅር” በጃፓን ለገበያ መቅረቡ ተሰምቷል።
የሩቅ እይታ ችግር “ማዮፒያ” የአይን ችግር ያለባቸው ሰዎች በቅርበት ያለን ነገር በትክክል ማየት የሚችሉ እና ነገሮች ከእነሱ እየራቁ ሲሄዱ በዥታ ብቻ የማየት ችግር ነው።
ይህ የአይን የእይታ ችግር (ማዮፒያ) መነሻ በባዛት ከአካባያዊ ችግር ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ አብዛኛውን ሰዓት በቤት ውስጥ ከማሳለፍ ጋር በተያያዘ በቂ ብርሃን ተፈጥሯው ብርሃን ካለማግኘት ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።
እንዲሁም በርካታ ሰዓትን በቤት ውስጥ በቴሌቪዥን፣ በኮምፒውተር እና ሌሎች የኤሌክትሮኒስክ እቃዎች ላይ የሚያሳልፉ ሰዎችም ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ይህ የአይን ችግር አስጊ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ይህንን የእይታ ችግር ለመቅረፍ ያለው አማራጭ እይታን የሚያስተካክል መነፅር አሊያም በአይን ብሌን ላይ የሚለጠፍ (ኮንታክት ሌንስ) መጠቀም ብቻ እንደሆነ ይነገራል።
አሁን ላይ ግን የጃፓኑ ኩቦታ ፋርማሲቲዩካልስ ኩባያ ይህንን የእይታ ችግር እስከወዲያኛው ሊቀርፍ የሚችል አዲስ ቴክኖሎጂ ይዞ መምጣጡን አስታውቋል።
ኩቦታ ፋርማሲቲዩካልስ ይህንን የእይታ ችግር ለማከም የሚያስችል ልዩ መነፅር ይዞ መምጣቱን ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ነበር ያስታወቀው።
መነጸሩ በብርሃን እጦት አማካኝነት ስራ አቁመው የችግሩ መንስዔ የሆኑ ሬቲናዎችን በቂ ብርሃ እንዲያገኙ እና እንዲነቃቁ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
ይህንን የእይታ ችግር ለመቅረፍም መነጸሩን በቀን ከ60 እስከ 90 ደቂቃ ብቻ ማድረግ በቂ እንደሆነም ኩባያው አስታውቋል።
መነጸሩ አሁን ላይ ለገበያ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙሩም 20 ፍሬ መነጽር ተመርቶ ለገበያ መቅረቡ ተውቋል።
አንዱ መነፅር በ 5700 የአሜሪካ ዶላር ወይም 770 ሺህ የጃፓን የን ለገበያ መቅረቡም ተነግሯል።
መነፅሩ አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ ብቻ ተመርቶ ገበያ ላይ በመዋሉ ዋጋው እንደተወደደ እና በኋላ ላይ በስፋት ወደ ምርት ሲገባ ዋጋው እንደሚቀንስ ታውቋል።