ፖለቲካ
ከአልኮል መጠጦች የማገኘው ገቢ ቀንሶብኛል ያለችው ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ማበረታታት ጀመረች
አልኮል መጠጦችን አምራች የሃገሪቱ ተቋማት ጭምር በሁኔታው መቸገራቸው ተገልጿል
የሀገሪቱ ገቢዎች ባለስልጣን ወጣቶች እንዲጠጡ በማበረታታት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል
ከአልኮል መጠጦች የማገኘው የገቢ ግብር ቀነሰብኝ ያለችው ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ማበረታታት ጀመረች።
ጃፓን ይህን የምታደርገው ከዘርፉ ይገኝ የነበረው ገቢ በማሽቆልቆሉ ምክንያት ነው።
ሁኔታው ከፍተኛ ግብር ከፋይ ለሆኑ የሃገሪቱ አልኮል አምራች ተቋማት ጭምር ራስምታት ሆኗል።
የገበያው መቀዛቀዝ ያሰጋቸው አንዳንድ ተቋማትም የአሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ገበያዎችን በማማተር ላይ ናቸው እንደ ሮይተርስ ዘገባ።
ሁኔታው እኔንም አሳስቦኛል ያለው የሃገሪቱ ገቢዎች ባለስልጣን ወጣቶች እንዲጠጡ በማበረታታት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል።
ተቋሙ በሁኔታው እየተቸገሩ ያሉ የአልኮል መጠጦችን አምራች ተቋማትን ጭምር ምክር ጠይቋል።
እርምጃው ከኮሮና ወረርሽኝ፣ ከእድሜ መግፋት እና በአጠቃላይም ከህዝብ ቁጥር መቀነስ ጋር በተያያዘ የተቀዛቀዘውን የዘርፉን እንዱስትሪ ለማነቃቃት ያስችላልም ተብሎለታል።
ሆኖም እርምጃው ከጤና ይልቅ ገቢን ያስቀደመ ነው በሚል በብዙዎች ተተችቷል።