ለኮፕ28 ፕሬዝዳንት የተጻፈ አለማቀፍ መልዕክት
የ28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ከ800 በላይ የሴክተር መሪዎች ፊርማቸውን ያሳረፉበትን መልዕክት ተቀብለዋል
መልዕክቱ ኤምሬትሱ ስኬታማ ጉባኤ የምድራችን መጻኢ ለመወሰን ታሪካዊ አሻራ ያሳረፈ ነው ይላል
የአረብ ኤምሬትስ የኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ዶክተር ሱልጣን አልጀበር ከአለማቀፍ መሪዎችና ተቋማት የእውቅና መልዕክት ተቀበሉ።
ከ800 በላይ የሴክተር መሪዎች ፊርማቸውን ያሳረፉበትን የእውቅና መልዕክት የኮፕ28 ፕሬዝዳንት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና እና አድናቆት የሰፈረበት ነው።
ከፈራሚዎቹ ውስጥ 300 አለምአቀፍ ስራ አስፈጻሚዎች፣ 34 የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም 20 አለምአቀፍ መሪዎች ይገኙበታል።
“ትጋትና ቁርጠኝነትዎን እናደንቃለን፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚከናወኑ ስራዎች በእጥፍ እንዲያድጉ እያደረጉት ያለውን ጥረት እንደግፋለን” ብለዋል መሪዎቹ።
የኮፕ28 ጉባኤ አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል የሚለው መልዕክቱ፥ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ለድርድር ከመቀመጥ የተደረሱ ስምምነቶች ተፈጻሚ የሚለው ሞዴል የሚደነቅ መሆኑን ያብራራል።
የኤምሬትሱ ስኬታማ ጉባኤ የምድራችን መጻኢ ለመወሰን ታሪካዊ አሻራ ያሳረፈ ስለመሆኑም የእውቅና ደብዳቤው ጠቁሟል።