የኮፕ28 ውሳኔዎች የዓለም ህጻናት የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ተባለ
የአየር ንብረት ለውጥ ህጻናትን የበለጠ ተጋላጭ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል
የዘንድሮው የተመድ ኮፕ 28 አየር ንብረት ለውጥ በዱባይ እየተካሄደ ይገኛል
የኮፕ28 ውሳኔዎች የዓለም ህጻናት የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ተባለ፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ 10ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ ምክክሮች እና ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ካሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የዓለም ህጻናት አድን ድርጅት አንዱ ሲሆን ኮፕ28 ጉባኤ ህጻናት የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያስችል ውሳኔ እንደተላለፈበት አስታውቋል፡፡
የተቋሙ ዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ካርላ ሃዳድ ማርዲኒ እንዳሉት ህጻናትን ለመደገፍ ከዓለም ተቋማት የሚመጣ የኢንቨስትመንት ፈንድ አነድ በመቶ ብቻ ለአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ ይውላል ብለዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ በየጊዜው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሱ የህጻናት ጉዳትን መቀነስ የሚያስችል እንደሆነም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡