መፈንቅለ መንግስት አድራጊው የሱዳን ጄነራል አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ
በቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል
ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ምክር ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል
መፈንቅለ መንግስት አድራጊው የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት አቋቋሙ፡፡
ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡
አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ምክር ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡
ሱዳን፤ አስገዳጅ ሁኔታ እስካልገጠማቸው ድረስ ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳሰበች
ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን በምክትልነት ሲመሩ የነበሩት ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳገሎ (ሄሚቴ)ም በአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪነት እንደሚቀጥሉም ቡርሃን አስታውቀዋል፡፡
ከ15ቱ የምክር ቤቱ አባላት መካከልም አምስቱ የሃገሪቱ ጦር መሪ ጄነራሎች ናቸው፡፡
የሱዳን ጦር ከ20 ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሚመራው የሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡
መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎም የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ስልጣኑ እንዲመለስ ሱዳናውያን በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
የሱዳን ሲቪል ጥምረት ከወታደራዊ ኃይሉ ጋር የሚደረገውን ድርድር ውድቅ አደረገ
አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎች አገራት የሱዳን ጦር ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድሩ እንዲመልስ በመወትወት ላይም ይገኛሉ፡፡
በርካታ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ተቋማትም ወታደሩ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድሩ ካላስረከበ የገንዘብ ብድር እና ሌሎች ድጋፎችን እንደማያደርጉ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
ቡርሀን ከሰሞኑ ከሽግግር በኋላ በሱዳን በሚመሰረተው አዲስ መንግስት ውስጥ ተሳትፎ አይኖረኝም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።