እየተጠናቀቀ ባለው የ2023 ዓመት በኢንተርኔት ላይ በብዛት የተፈለጉ ሰዎች እና ቀላቶች ይፋ ተደርገዋል
በ2023 በኢንተርኔት ላይ በብዛት የተፈለጉ ሰዎች እነማን ናቸው?
የፈረንጆቹ 2023 ከገባ የመጨረሻው ወር ላይ ሲሆን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የገና በዓልን በመቀጠልም አዲስ አመታቸውን ያከብራሉ፡፡
በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ውስጥ ዓለምን አንድ በሚያደርገው በኢንተርኔት ላይ በብዛት የተፈለጉ ግለሰቦች፣ ፖለቲከኞች፣ ቃላቶች እና በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች ሪፖርት ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህ ሪፖርት መሰረት ዩቲዩብ በመላው ዓለም ብዙ ፈላጊ ያለው ተቋም የተባለ ሲሆን በመቀጠልም ፌስቡክ፣ዋትስአፕ ዌብ፣የአየር ንብረት፣ ትርጉም፣ ጎግል፣ አማዞን፣ ጂሜይል፣ ጎግል ትራንስሌት እና ኢንስታግራም በቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 10 ኛ ድረስ ያለውን ይዘዋል፡፡
በግለሰብ ደረጃ ደግሞ አሜሪካዊቷ ድምጻዊት ቴይለር ስዊፍት በዓመቱ በብዛት ኢንተርኔት ላይ የተፈለገች ቀዳሚ ሰው ስትሆን፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣፣ቼር፣ድሬክ፣ አሸር፣ዶናልድ ትራምፕ፣ አዳም ሳንድለር፣ ኦሊቪያ ሮድሪጎ እና ኤለን መስክ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ እንደያዙ ግልመፕስ የተሰኘው የመረጃ እና ትንታኔ ተቋም ይፋ አድርጓል፡፡
95 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ጎግልን ይጠቀማሉ የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ቢንግ እና ያሁን መረጃዎችን ከበይነ መረብ ለማግኘት እንደ አማራጭ ይጠቀማሉ፡፡
“ዋት“ የምትለዋ የእንግሊዘኛ ቃል ደግሞ ኢትዮጵያዊያን አብዝተው የሚጠቀሟት ቃል ነች የተባለ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ “ኢትዮጵያ፣ ዋት ኢዝ፣ ትራንስሌት እና ጎግል“ የተሰኙ ቃላቶች ደግሞ በቅደም ተከተላቸው ኢትዮጵያዊያን በመረጃ ሰጪ የበይነ መረብ ገጾች ላይ የሚጽፏቸው ቃላት እንደሆኑም ተገልጿል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት ዊል ስሚዝ በበይነ መረብ ላይ በብዛት የተፈለገው ሰው ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን በ2021 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም በ2020 ኮብ ብሪያንት ተፈላጊው ሰው ተብለው ነበር፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በታሪክ በብዛት በበይነ መረብ ገጾች ላይ የተፈለጉ ሰው ሲሆኑ ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ አራት ጊዜ የዓመቱ ተፈላጊው ሰው ተብለዋል፡፡