የኢራኑ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ሁከትና ሽብር እንዲፈጠር አድርገዋል ሲሉ ከሰሱ
በሀገሪቱ በተለይም በኩርድ ግዛቶች ከፍተኛ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን በተቃውሞው ወቅትም በርካታ ሰዎች ተገድለዋል
በኢራን ተቃውሞ የተነሳው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያለች የኩርድ ሴት ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ ነበር
የኢራኑ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ራይሲ አራት ሳምንታት ባስቆጠረው የኢራን ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ የአሜሪካ አቻቸውን “ሁከት፣ ሽብር እና ውድመት” እንዲፈጠር በመቀስቀስ ከሰዋል፡፡
ረኢሲ ጆ ባይደን የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች በኢራን ብጥብጥ፣ ሸብር እና ውድመት ማስከተላቸው የኢራን እስላሚክ ሪፐብክ መስራች አሜሪካን “ታላቅ ሰይጣን” ማታቸውን ያስታወሰናል ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ባይደን ኢራን መብታቸውን በጠየቁ ዜጎቿ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ታቁም የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ይህ አስተያየት በአራኑ ፕሬዝደንት ዘንድ በበጎ አልተወሰደላቸውም፡፡
በኢራን ተቃውሞ የተነሳው የ22 አመቷ ኩርድ ሴት ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ለብሰሻል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ ነው፡፡
በሀገሪቱ በተለይም በኩርድ ግዛቶች ከፍተኛ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን በተቃውሞው ወቅትም በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፤ ቆስለዋል፡፡ የኢራን ፖሊስም ሁከት ፈጥረዋል ያላቸውን 100 ሰዎችን ከሷል፡፡
አሜሪካ በኢራን የተነሳውን ተቃውሞ እየተጠቀመችበት መሆኑን ስትገልጽ የነበረችው ህወሃት በኢራን ላይ የማተራመስ ፖሊሲ እየተከተለች ነው ስትል ክስ ማሰማቷ ይታወሳል፡፡