የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፤ ሩሲያ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጥቃት እያደረሰችብን ነው አሉ
ጥቃቱ ፕሬዝዳንተ ፑቲን በክራይሚያ ከርች ድልድይ ለደረሰው ውድመት ዩክሬንን ተጠያቂ ካደረጉ በኋላ የተሰነዘረ ነው
እካሁን ድርስ ቢያንስ 75 የሩሲያ ሚሳዔሎች በዩክሬን የተለያዩ ከተሞች ጥቃት ማድረሳቸውንም የዩክሬን ጦር አስታውቋል
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ፤ሩሲያ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጥቃት እያደረሰችብን ነው አሉ፡፡
ጥቃቱ ዛሬ ጠዋት የተሰነዘረና በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ላይ ያነጣጠረ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የዩክሬን የኢነርጂ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
"ዛሬ ጠዋት አስቸጋሪ ነው፤ ከአሸባሪዎች ጋር እየገጠምን ነው፤ በደርዘን ከሚቆጠሩ ሚሳኤሎች እና የኢራን ሻሄዶች( ሰው አልባ የውጊያ አውሮፕማኖች)… ሁለት ኢላማዎች አሏቸው፤ በመላው ሀገሪቱ የኃይል ተቋማትን ... ሽብር እና ትርምስ መፍጠር፤ የኃይል መሰረተ ልማታችንን ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ ሁለተኛው ኢላማ ሰዎች ናቸው" ሲሉም ነው ዘለንስኪ በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ ቪዲዮ የተናገሩት፡፡
እካሁን ድርስ ኪቭን ጨምሮ በደቡብና ምዕራብ ዩክሬን ቢያንስ 75 የሩሲያ ሚሳዔሎች ጥቃት ማድረሳቸውንም የዩክሬን ጦር መግለጹም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአሁን ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ሚሳዔሎች ድብደባ የጦርነቱ መጀመሪያ አከባቢ ሞስኮ ኪቭን ለመቆጣጠር ታደርገው የነበረ መጠነ ሰፊ ጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡
የክሬምሊን ባለስልጣናት በሰው አልባ እውሮፐላኖች ደርሷል ስለተባለው ጥቃት እስከሁን ያሉት ነገር ባይኖርም፤ ጥቃቱ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በክራይሚያ ከርች ድልድይ ለደረሰውን ፍንዳታ ዩክሬንን በሽብርተኝነት ተጠየቂ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተሰነዘረ ነው፡፡
ፑቲን “ምንም ጥርጥር የለም፤ ይህ ወሳኝ የሆኑ የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ለማጥፋት ያለመ የሽብር ተግባር ነው" ሲሉ እሁድ እለት በክሬምሊን የቴሌግራም ቻናል ላይ በተለጠፈው ቪዲዮ ላይ ተናግረዋል።
ይህ ሆን ተብሎ በትእዛዝ የተከናወነ ነውም ማለታቸውንም የኤኤፍፒ ዘገባ ያመለክታል፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዝዳንትና የሀገሪቱ የደህንነት ም/ቤት ምክትል ኃለፊ ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ሩሲያ "አሸባሪዎችን" መግደል አለባት ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
“ሩሲያ ለዚህ ወንጀል ምላሽ መስጠት የምትችለው አሸባሪዎችን በቀጥታ በመግደል ብቻ ነው፣ በሌላው ዓለም እንደተለመደው፤ ይህ የሩሲያ ዜጎች የሚጠብቁት ነው " ሲሉም ነው የተናገሩት ሜድቬዴቭ፡፡
የክሬምሊን ባለስልጣናት ይህን ቢሉም ግን ለድለድዩ መውደም በኪቭ ባለስልጣናት በኩል በግልጽ ተባለ ነገር የለም፡፡
ነገር ግን የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር የድልድዩን ፍንዳታ በሚያዝያ ወር ከሰጠመችው የሩስያዋ ሞስኮቫ የሚሳኤል መርከብ ጋር አነጻጽሮታል።
"በዩክሬን ክሬሚያ ውስጥ የነበሩ ሁለት ታዋቂ የሩሲያ የታላቅነት ምልክቶች ወድመዋል። በቀጣይስ ምን አለ?" ሲልም በትዊተር ገጹ አስፍረዋል፡፡
የዩክሬን መንግስትም እንዲሁ በትዊተር ገጹ “ተቃጥሏል” የሚል ጽሁፍ አጋርቷል፡፡
የዩክሬን ባለስልጣናት ባህረ ሰላጤውን (የክሬሚያ ግዛትን) መልሰው ለመውሰድ ቃል ስለገቡ ይህ ትክክለኛ ዒላማ ነውም ብሏል።
ከፍተኛ የሩስያ ጦር ባለባት በክሬሚያ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት ለክሬምሊን ሌላ ትልቅ ውርደት ተደርጎ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።
እናም የአሁኑ ሩሲያ ፈጸመችው በሚል እየቀረበ ያለው ክስ የአጸፋ ምት ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡