ኢራን፤ አሜሪካ በኢራን የተቀሰቀሰውን አለመረጋጋት ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ እየተጠቀመችበት ነው ስትል ከሰሰች
በኢራን ተቃውሞ የተቀሰቀሰው ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ለብሳለች የተባለች ሴት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች መሞቷን ተከትሎ ነው
ኢራን የታጠቁ የኢራናውያን የኩርድ ተቃዋሚዎችን በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው አለመረጋጋት እጃቸው እንዳለበት ስትል ወቅሳለች
አሜሪካ ባለፈው ሰኞ በኢራን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች በሞተችው ሴት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ሀገሪቱን ለማተራመስ ተጠቅማለች ስትል ከሰሰች፡፡
ከፈረንጆቹ 2019 ወዲህ የተስተዋለው ትልቁ አለመረጋጋት የመቀነስ ምልክት ባለማሳየት ኢራንም ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቃለች፡፡
ኢራን 22 ዓመቷ ኩርዳዊት ሴት መህሳ አሚኒ በሴቶች አለባበስ ላይ የጣለውን ጥብቅ ገደቦች ጥሳለች በሚል በፖሊስ ከታሰረች በኋላ መሞቷ ተከትሎ በተቀሰቀሱ ህዝባዊ ሰልፎች እየተናጠች ነው፡፡
ጉዳዩ በሀገሪቱ ላይ አለም አቀፍ ውግዘት ማስከተሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኢራን መንግስት ሁከት ፈጣሪዎችን በመገደፍ እስላማዊ ሪፐብሊክ የሆነችውን ኢራን ለማተራመስ ትጥራለች ብሏል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ በመግለጫው ላይ "ዋሽንግተን የኢራንን መረጋጋት እና ደህንነት ለማዳከም ሁልጊዜ እየሞከረ ነው" ብለዋል ።
ካናኒ በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ እንገለጹት አሜሪካ እና አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት መሪዎችን "ሁከት ፈጣሪዎችን" በመደገፍ አንድ አሳዛኝ ክስተት አላግባብ በመጠቀም እና "በአገሪቱ ጎዳናዎች እና አደባባዮች ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስርዓቱን በመደገፍ ላይ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በደረንጆቹ መስከረም 17 በተጀመረው አመፅ ቢያንስ 41 ሰዎች መሞታቸውን የመንግስት ቲቪ ዘግቧል።
ምንም እንኳን በአሚኒ ሞት ላይ የተካሄዱት ሰልፎች ለመንግስት ትልቅ ፈተና ቢሆኑም ተንታኞች ለሀገሪቱ መሪዎች አፋጣኝ ስጋት አይሆኑም ምክንያቱም የኢራን የጸጥታ ሃይሎች ቀደም ሲል ተቃውሞዎችን አስወግደዋል።
ኢራን የታጠቁ የኢራናውያን የኩርድ ተቃዋሚዎችን በሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው አለመረጋጋት እጃቸው እንዳለበት ወቅሳለች፡፡
የኢራን አብዮታዊ ጥበቃዎች በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የኩርዲሽ ክልል ውስጥ በሚገኙ የኢራን ታጣቂ ተቃዋሚ ሰፈሮች ላይ የመድፍ እና የድሮን ጥቃት መፈፀማቸውን ከፊል ኦፊሴላዊ የታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።