በኢራን የአረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ሰይድ መሃመድ አልዛቢ በቀናት ውስጥ በቴህራን ስራቸውን ይጀምራሉ
በኢራን የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ወደ ቴህራን በማቅናት ዳግም ስራ ሊጀምሩ እንደሆነ ተገለጸ።
ኢራን ለአሜሪካ ወዳጅ ከሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር ግንኙነቷ ተበላሽቶ መቆየቱ ይታወሳል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከነዚህ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን አሁን ላይ ከኢራን ጋር ያላት ወዳጅነት መሻሻሉን ተከትሎ በቴህራን የአረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ዳግም ስራ ሊጀምሩ መሆኑን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
አረብ ኢምሬት እና ኢራን ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማሻሻል ላይ ሲሆኑ አቡዳቢ በቴህራን በሚገኘው ኢምባሲዋ አምባሳደር መሾሟ ተገልጿል።
አዲሱ የአረብ ኢምሬት አምባሳደር ሰይድ መሃመድ አልዛቢ በቀጣይ ቀናት ውስጥ ወደ ቴህራን አቅንተው ስራቸውን እንደሚጀምሩ የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
ኢራን ከአረብ ኢምሬት እና ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማሻሻል ላይ ስትሆን አሜሪካ ጋር በፈረንጆቹ 2015 ላይ የተደረገውን የኑክሌር ስምምነት ለማስቀጠል በኦስትሪያ በመወያየት ላይ ናቸው።