እስራኤል፤ በኢራን የኒውክለር ጉዳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ተቃወመች
ሊደረስ የሚችለውን ስምምነት እንደማትቀበልና እንደማይመለከታትም ገልጻለች
ጠቅላይ ሚኒስትር ላፒድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ጋር በጉዳዩ ላይ ተነጋግረዋል
እስራኤል፤ በኢራን የኒውክለር ጉዳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ተቃወመች።
በጉዳዩ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደማትቀበል እና እንደማይመለከቷትም ገልጻለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዬር ላፒድ ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ጉዳዩን በተመለከተ በስልክ አውርተዋል።
በንግግራቸው ሃገራቸው ኢራን በፍጹም ኒውክለር እንድትታጠቅ እንደማትፈቅድ ያሳወቁት ላፒድ ይህ እንዳይሆን የትኛውንም ነገር እናደርጋለን ሲሉ ብለዋል።
ከአሁን ቀደም (በ2015) ስምምነት ተደርሶበት በነበረው የኢራን የኒውክለር ጉዳይ ላይ በድጋሚ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
አሜሪካ በቀድሞ ፕሬዝዳንቷ ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ከስምምነቱ መውጣቷ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ጉዳዩ የተቀዛቀዘ ቢመስልም ኢራን ኒውክለር ለመታጠቅ በሚያስችል ደረጃ ከፍተኛ መጠን ያለው ዩራኒየም ማበልጸጓን ቀጥላለች። ይህን ተከትሎም አውሮፓውያን ወደ ስምምነቱ ለመመለስ የሚመስላቸውን ድርድር በድጋሚ ማካሄድ ጀምረዋል።
ድርድሩ ፈር እየያዘ ነው በተባለበት ሁኔታም ነው እስራኤል የተቃወመችው።
የድርድሩ ውጤት እንደማይመለከታትና የድርድሩ አካል እንደማትሆንም በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ገልጻለች።
ዬር ላፒድ ቴህራን ኒውክለር እንዳትታጠቅ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ኃያላኑ በድጋሚ ከቴህራን ተደራዳሪዎች ጋር ተገናኝተው ለድርድር ይቀመጣሉ የሚል እምነት እንደሌላቸውም ነው የገለፁት።
ፕሬዝዳንት ማክሮንም ኒውክለር እንድትታጠቅ እንደማይፈቅዱና ይህ እንዳይሆን ለማድረግ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።