በ2023 የአለም ሀገራት ለመከላከያ የመደቡት አጠቃላይ ገንዘብ ከ2.4 ትሪሊየን ዶላር ተሻግሯል
በመካከለኛው ምስራቅ እያየለ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ ሀገራት ምን ያህል ወታደራዊ አቅም አላቸው የሚለው ጥያቄ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
በቀጠናው ለረጅም ጊዜ በጠላትነት የሚተያዩት ኢራን እና እስራኤል በአካባቢው በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ከፍተኛ የጦር መሳርያዎችን ከታጠቁ ግንባር ቀደም ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የሀገራትን ወታደራዊ አቅም እና ጥንካሬ የሚመዘግበው ግሎባል ፋየር ፓዎር ባወጣው መረጃ መሰረት ሁለቱ ተቀናቃኞች ተጻራሪ ጥንካሬ እንዳላቸው አመላክቷል፡፡
ለአብነት ኢራን በርካታ የወታደር ቁጥር ከፍተኛ የምድር ውጊያ አቅም ሲኖራት በአንጻሩ እስራኤል በቴክኖሎጂ እድገት እና በስትራቴጂካዊ ጥምረት የላቀች ናት።
ምንም እንኳን ሀገራቱ እንደሚዋጉበት የጦር ሜዳ አውድ ወታደራዊ አቅማቸው የሚኖረው ጠቀሜታ ቢለያይም አንድኛው ከሌላኛው የሚሻልባቸው ወታደራዊ ጥንካሬዎች መኖራቸውን መረጃው ጠቁሟል፡፡
በህዝብ ቁጥር ደረጃ ኢራን 88.5 ሚሊየን ህዝብ ሲኖራት እስራኤል 9.5 ሚሊየን ዜጎች ባለቤት ናት፡፡
ሊዋጉ የሚችሉ ዜጎችን ቁጥር የተመለከትን እንደሆነ 49 ሚሊየን ለመዋጋት ብቁ የሆነ ዜጋ ያላት ቴሄራን 3.8 ሚሊየን ከያዘችው ቴልአቪቭ የተሻለች ናት፡፡
በሰራዊት ቁጥር ሁለቱ ሀገራት በመቶ ሺዎች ልዩነት አላቸው። ኢራን 610 ሺህ ወታደሮችን ከ350 ሺህ ተጠባባቂ ጦር ጋር የያዘች ሲሆን እስራኤል በበኩሏ 170 ሺህ ወታደር እና 465 ሺህ ተጠባባቂ ጦር አላት፡፡
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ሀገራት ለወታደራዊ ወጪዎች የሚይዙት በጀት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል፡፡
ለወትሮው በተለምዶ በጦር መሳርያ ፉክክር ውስጥ የሚገኙ ሀያላን ሀገራት ከሚያወጡት ገንዘብ በተጨማሪ ተጨባጭ ስጋት አለብን ያሉ የአለም ክፍሎች ጦራቸውን ለማዘመን በቢሊየን ዶላሮች ወጪ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በዚህም በ2023 አጠቃላይ የአለም ወታደራዊ ወጪ 2.4 ትሪሊየን ዶላር መሻገሩን መረጃዎች ያሳያሉ
ንጽጽሩን የሚያሳየውን የግሎባል ፋየር ፓወር መረጃ ከስር ካለው ምስል ይመልከቱ፡፡