ስለኢራን ድሮኖች እስካሁን የምናውቀው
ኢራን “ሻሄድ - 136” እና “አባቢል - 2” የተሰኙትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን በማምረት ላይ ትገኛለች
የቴህራን ድሮኖች በኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊባኖስ እና የመን በሚካሄዱ ውጊያዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው
ኢራን በአሜሪካና በመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቿ ላይ ጥቃት የምትፈጽምባቸውን ዘመናዊ ድሮኖች በማምረት ላይ ትገኛለች።
ቴህራን “ሻሄድ” እና “አባቢል” የተሰኙትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስና እጅግ ዘመናዊ ድሮኖችን መታጠቋም ተገልጿል።
ኢራን ሰው አልባ አነሰተኛ አውሮፕላኖቹን ከየመን እስከ ሶሪያ፤ ከኢራቅ እስከ ሊባኖስ ለምታስታጥቃቸው ሃይሎች መላኳንም መረጃዎች ያመላክታሉ።
የቴህራን ድሮኖች ውጤታማነት በየጊዜው እየተሻሻለ መሄድ እስራኤልን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገዳደሯት ሃይሎች ስጋት ፈጥሯል።
የኢራን ዋና ዋና ድሮኖች የትኞቹ ናቸው?
“ሻሄድ 136”
- ይፋ የተደረገው በ2021
- እስከ 2 ሺህ 500 ኪሎሜትር መጓዝ ይችላል (እስራኤልን መምታት ይችላል)
- በስአት 185 ኪሎሜትር ይጓዛል
- 50 ኪሎግራም የሚመዝን ፈንጂ መሸከም ይችላል
“አባቢል 2”
- ለቅኝት፣ ስለላና ጥቃት
- በአየር ላይ ለአንድ ስአት ከ50 ደቂቃ መቆየት ይችላል
- እስከ 900 ኪሎሜትር በመጓዝ 770 ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ቦታን ይቃኛል
- ከጀልባዎች ላይ ሊተኮስ ይችላል
- ከ2022 ጀምሮ በታጂኪስታን እየተመረተ ነው
- “አባቢል- 1” ከ1980 እስከ 1988 በተካሄደው የኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ጥቅም ላይ ውሏል
“ሲሞርግ” ወይም “ሻሄድ 171”
- በ2017 ተዋወቀ
- ዲዛይኑ በ2011 በኢራን አየር ክልል ከገባው የአሜሪካው “አርኪው-170” የተወሰደ ነው
- በ4 ሺህ 400 ኪሎሜትር ርቀት ጥቃት ማድረስ ይችላል
- ከፍተኛ ፍጥነቱ በስአት 460 ኪሎሜትር
- 100 ኪሎግራም የሚመዝኑ ቦምቦች ይሸከማል
- በ36 ሺህ ጫማ ከፍታ ለ10 ስአታት ያለማቋረጥ መጓዝ ይችላል
“አራሽ”
- በ2019 ተዋወቀ
- መጓዝ የሚችለው ርቀት 2 ሺህ ኪሎሜትር
- አየር ላይ መቆየት የሚችለው 8 ስአት ከ50 ደቂቃ
- መሸከም የሚችለው ፈንጂ ክብደት 30 ኪሎግራም
- በባህር ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ ወደመጣበት ይመለሳል
“ፎትሮስ”
- ይፋ ተደረገ በ2013
- በ25 ሺህ ጫማ ከፍታ ለ30 ስአታት ያለማቋረጥ መጓዝ፣
- ከቁጥጥር ክፍል እስከ 2 ሺህ ኪሎሜተር ተጉዞ ኢላማ መምታት ፣
- በስአት 250 ኪሎሜትር መጓዝ፣
- አራት ሚሳኤሎች እና ቦምቦች መጫን ይችላል።
“ሞሃጄር 6”
- በመጋቢት 2017 ተዋወቀ
- በሀምሌ 2019 ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ዋለ
- ጥቃት ሊያደርስበት የሚችለው ርቀት 2000 ኪሎሜትር
- ፍጥነት በስአት 200 ኪሎሜትር
- ለ12 ስአታት በ18 ሺህ ጫማ ከፍታ ያለማቋረጥ መብረር፤
- ከ100 እስከ 150 ኪሎግራም የሚመዝኑ የጦር መሳሪያዎችን መሸከም ይችላል።
ኢራን ከትናንት በስቲያ ወደ እስራኤል ጥቃት ስታደርስ በርካታ ድሮኖችን ተጠቅማለች።
በተለይ “ሻሄድ 136” እና “ሻሄድ - 131ኤስ” የተሰኙት ድሮኖች በብዛት ጥቅም ላይ መዋላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የኢራን ድሮኖች እጅግ ፈጣን አለመሆናቸው በእስራኤል እይታ ውስጥ ገብተው በመቃወሚያዎች ተመተው እንዲወድቁ እንዳደረጋቸው ተንታኞች ያነሳሉ።