“አል-ዛዋሪ” ስለ “ፈጣኑና አደገኛው” የሃማስ ድሮን ምን ያክል ያውቃሉ?
ሃማስ በእስራኤል ላይ በከፈተው ጥቃት ከሮክት በተጨማሪ ድሮን እየተጠቀመ ነው
ሃማስ አደገኛ የተባሉትን 35 አል ዛዋሪ ድሮኖች በሁሉም ግንባር አሰማርቷል
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።
ሃማስ እስራኤል ላይ በሮኬት እንዲሁም ተዋጊዎቹ በፓራሹትና በተለያዩ መንገዶች ድንበር ጥሰው ገብተው ወረራ ያደረገ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም “አል-ዛዋሪ” የተባለ በድሮን ጥቃት እየሰነዘረ ነው።
ሃማስ የድሮን ጥቃት እየፈፀመ ያለው “አል-ዛዋሪ” የሚል መጠሪያ ባለው “ፈጣን እና አደገኛ” ድሮን መሆኑም ታውቋል
“አል-ዛዋሪ”የርቀት መቆጣጠሪያ (ሪ፣ት ኮንትሮል) የሚሰራ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ሲሆን፤ ሃማስ ለውጊያ መሳሪያነት የሚጠቀምበት ፈጣኑ የጦር መሳሪያ ነው።
ድሮኑ እንደ ፈንጂ ያሉ የጦር መሳሪያዎችን በመታጠቅ የማቅረብ አቅም ያለው ሲሆን በእስራኤል ኢላማዎች ላይ ለማጥቃት ሲውል ቆይቷል።
አል-ዞዋሪ የአጥፍቶ ጠፊ ድሮን በጠንካራው የእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት “አይረን ዶም” ሊያቆመው አይችልም ተብሏል።
ሃማስ በሁሉም ግንባር 35 አል ዛዋሪ ድሮን ማሰማራቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ድሮኖቹ በተለያዩ የእስራኤል ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፣
ድሮኑ “አል-ዙዋሪ” የሚል ስያሜ ተሰጠው በፈረንጆቹ በ2016 በእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድ በተገደለው በሐማስ ወታደራዊ ክንፍ መሪ መሐመድ አል-ዛዋሪ ስም ነው።
ሃማስ ቡድን እስራኤል ላይ ለምን ጥቃት ከፈተ?
የሃማስ ቃል አቀባይ ካሊድ ካዶሚ በበኩሉ፤ ቡድኑ በእስራኤል ላይ የጀመረው ወታደራዊ ዘመቻ ባለፉት አስርት ዓመታት ፍልስጤማውያን ላይ ለተፈጸመው ግፍ ምላሽ ነው ብሏል።
“ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በጋዛ የሚፈጸመውን ግፍ እንዲያስቆም እንፈልጋለን” ያለው ቃል አቀባዩ፤ “አል ኣቀሳን ጨምሮ ቅዱሳን ስፍራዎቻችን ለዘመቻው መጀመር መነሻ ነው” ብሏል።
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል በተጀመረው ጦርነት ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ 500 ማለፉ ተነግሯል።