ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በስቅላት ቀጣች
ግለሰቡ ወጣት ሴቶችን አገባችኋለሁ በሚል ማታለያ ሲደፍር ነበር ተብሏል
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የሆኑ ሰዎችን በስቅላት እንዲቀጡ የሚፈቅድ ህግ አላት
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በስቅላት ቀጣች፡፡
የመካከለኛ መስራቋ ሀገር ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በአደባባይ ላይ በስቅላት ገድላለች፡፡
ሞሀመድ አሊ የተባለው ይህ ኢራናዊ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በርካታ ሴቶች እንደሚያገባቸው ቃል በመግባት አስገድዶ ደፍሯቸዋል ተብሏል፡፡
ግለሰቡ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በተከሰሰበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ትፋተኛ ሆኖ እንደተገኘ አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ መሀመድ አሊ ከ10 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከእሱ የጸነሱትን ልጅ እንዲያስወርዱ መድሃኒት ሰጥቷልም ተብሏል፡፡
በምዕራባዊ ኢራን ክፍል በምትገኘው ሀሜዳን ከተማ የሚኖረው ይህ ሰው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 200 ሴቶች ደፍሮናል ሲሉ ክስ መስርተውበት ነበር፡፡
በግለሰቡ ተደፍረናል ያሉ ሴቶች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍም ተደርጎበት ነበር፡፡
ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ቀጣች
ኢራን በየጊዜው በርካታ ዜጎች በስቅላት ከሚቀጡባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ተመድን ጨምሮ በርካታ ሰብዓዊ ድርጅቶች የሞት ቅጣት እንዲቀር በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከሆነ የሞት ፍርድ ቁጥር እየጨመረ የመጣ ቻይና ብዙ ዜጎቿን በስቅላት በመቅጣት ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ ዜጎችን ትገድላለች፡፡
ኢራን ደግሞ በየዓመቱ ከ570 በላይ ዜጎችን በስቅላት ስትቀጣ አፍሪካዊቷ ግብጽም ዜጎቿን በስቅላት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ተጠቅሳለች፡፡
ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር በተጨማሪነት የተጠቀሱ ሀገራት ሲሆኑ ሀገራቱ ዜጎቻቸውን በሞት እየቀጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡