ብዙ ዜጎቻቸውን በስቅላት የሚቀጡ ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ እና ግብጽ በአንጻራዊነት ብዙ ዜጎቻቸውን በስቅላት የቀጡ ሀገራት ናቸው
የሞት ቅጣት እንዲቀር የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት እየጠየቁ ናቸው
ብዙ ዜጎቻቸውን በስቅላት የሚቀጡ ሀገራት እነማን ናቸው?
እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከሆነ የሞት ፍርድ ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ፍርዳቸው በስቅላት ወይም አንገታቸው ተቀልቶ የሚገደሉ እንዳሉም ተገልጿል፡፡
በ2022 ዓመት ብቻ 2 ሀገራት ዜጎቻቸውን በስቅላት ቀጥተዋል የተባለ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ መከሰት በሞት የሚቀጡ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓልም ተብሏል፡፡
ቻይና ብዙ ዜጎቿን በስቅላትበመቅጣት ከዓለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን በዓመት በአማካኝ 1 ሺህ ዜጎችን በስቅላት ቀጥታለች፡፡
ሌላኛዋ ሀገር ኢራን ስትሆን ከ570 በላይ ዜጎችን በስቅላት ስትቀጣ አፍሪካዊቷ ግብጽም ዜጎቿን በስቅላት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ተጠቅሳለች፡፡
ሳውዲ አረቢያ፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር በተጨማሪነት የተጠቀሱ ሀገራት ሲሆኑ ሀገራቱ ዜጎቻቸውን በሞት እየቀጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡