በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት
ቻይና እና ሳውዲ አረቢያ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በሞት ከሚቀጡ ሀገራት መካከል ናቸው
አሜሪካንን ጨምሮ ስድስት የዓለማችን ሀገራት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት እንዲኮላሽ የሚፈቅድ ህግ አላቸው
በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከስቅላት እስከ ብልት ማኮላሸት የሚደርስ እርምጃ የሚወስዱ የዓለማችን ሀገራት
እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ትናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመላው ዓለም ያለ ክስተት ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ወንጀሉን ፈጽመዋል በተባሉ ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጅተዋል፡፡
በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ
በርካታ ዓለማችን ሀገራት የአስገድዶ መደፈር ወንጀልን ለመከላከል ወንጀለኛ መቅጫ ህጎችን ያዘጋጁ ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ግን ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣትን በመጣል ይታወቃሉ፡፡
ለአብነትም ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ፓኪስታን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ የወንድ ብልትን ከማምከን ጀምሮ በስቅላት እና በእሳት በማቃጠል እንዲገድሉ የሚፈቅድ ህግ አላቸው፡፡
አሜሪካ ካሏት ጠቅላላ ግዛቶች መካከል ሰባቱ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን ብልት ማምከን የሚያስችል ህግ ያላቸው ሲሆን በዚሁ ወንጀል እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ቶሎ ከእስር መለቀቅ ከፈለጉ ብልታቸው እንዲመክን መፍቀድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት በማቃጠል ህይወታቸው እንዲያልፍ የምታደርግ ሲሆን ግብጽ አንቆ በመግደል እንዲሁም ሳውዲ አረቢያ ደግሞ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት የሞት ፍርድ ትፈጽማለች፡፡
ፓኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዩክሬን፣ ቸክ ሪፐብሊክ እና ሌሎችም ሀገራት ዜጎቻቸውን ከወንጀል ለመጠበቅ ጥፋተኛ በተባሉ ዜጎች ላይ ጥብቅ ህግ ካላቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡