ስለ “ቃደር 1” ባለስቲክ ሚሳኤል እስካሁን የምናውቀው
ሄዝቦላህ በቴል አቪቭ አቅራቢያ ወደሚገኘው የሞሳድ ዋና ቢሮ ያስወነጨፈው ኢራን ሰራሹን “ቃደር 1” ሚሳኤል መሆኗን ገልጿል
ከምድር ወይንም ከባህር ላይ መወንጨፍ የሚችለው “ቃደር 1” ሚሳኤል የጦር መርከቦችን ጭምር ማውደም ይችላል ተብሏል
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ዛሬ ወደ እስራኤሉ የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) የተኮሰው ባለስቲክ ሚሳኤል “ቃደር 1” መሆኑን ገልጿል።
የሊባኖሱ ቡድን ጥቃቱን ያደረሰው የሬዲዮ መገናኛ መሳሪያዎች (ፔጀር) ጥቃቱ የተቀነባበረው በቴል አቪቭ በሚገኘው የሞሳድ ቢሮ ነው በሚል ነው።
የእስራኤል ጦር ዴቪድ ስሊንግ በተባለው የሚሳኤል መቃወሚያ ስርአት “ቃደር 1” ሚሳኤልን መትቶ መጣሉን ገልጿል። እስካሁን ሚሳኤሉ ስላደረሰው ጉዳት ግን የተባለ ነገር የለም።
የእስራኤል ጦር ዴቪድ ስሊንግ በተባለው የሚሳኤል መቃወሚያ ስርአት “ቃደር 1” ሚሳኤልን መትቶ መጣሉን ገልጿል። እስካሁን ሚሳኤሉ ስላደረሰው ጉዳት ግን የተባለ ነገር የለም።
ሄዝቦላህ የባህር ላይ ጥቃቶችን ለመፈጸም ይበልጥ ተመራጭ የሆነውን ሚሳኤል ወደ እስራኤል ያስወነጨፈው ለቴል አቪቭ ባለስቲክ መሳሪያ ታጥቄያለሁ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ተብሏል።
የ”ቃድር 1” ሚሳኤል አረር የጦር መርከቦችን ጭምር ከጥቅም ውጭ የማድረግ አቅም እንዳለውና በማደባየት አቅሙ በተደጋጋሚ የሚወደስ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ሚሳኤሉ በሶቪየት ሰራሹ ሚግ ሄሊኮፕተርም ሆነ በአሜሪካው “ኤፍ4 ፋንተም” የውጊያ አውሮፕላን ላይ ተገጥሞ በፍጥነት ኢላማውን መምታት ይችላል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ እና የኢራን ጦር በርካታ “ቃደር 1” ሚሳኤሎችን ታጥቀዋል ተብሏል።
“ቃደር 1” ባለስቲክ ሚሳኤል
- ኢራን ሰራሽ ነው
- ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገው መስከረም 2 2013 በቴህራን ነው
- ከ15 እስከ 16.5 ሜትር ይረዝማል
- አጠቃላይ ስፋቱ 1.25 ሜትር ነው
- ፍጥነት - በስአት ከ1100 ኪሎሜትር በላይ
- ከ200 እስከ 300 ኪሎሜትር ድረስ ይምዘገዘጋል
- ሁለት አይነት ነው፤ የምድር እና የባህር ሃይል
- ከባህር እና ከምድር ላይ መወንጨፍ ይችላል
- የጠላትን ራዳር በመለየት አቅጣጫ ለውጦ ጥቃት ያደርሳል
- በጣም ዝቅ ብሎ በመምዘግዘግ (ከባህር ወለል እስከ 3 ሜትር ብቻ ከፍ በማለት) ጥቃት ያደርሳል
- በሚሸከመው ቦምብ ክብደትና ኢላማውን በማደባየት አቅሙ ዝነኛ ነው
- የሚሳኤሉ አረር ክብደት ከ700 እስከ 1 ሺህ ኪሎግራም ይመዝናል