ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን ግዙፍ የባህር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማደረግ ጀመሩ
ልምምዱ በባህር ላይ መርከብና ድሮን ጨምሮ የጠላት ኢላማዎችን መምታት እንዲሁም ጉዳትን መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በተቃቃረችበት ማግስት የተጀመረው ልምምዱ በሶስቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው
ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን በኦማን ብህረ ሰላጤ ላይ ግዙፍ የሆነ የባህር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ መጀመራቸው ተገለጸ።
ሶስቱ ሀገራት መሰል የባህር ኃይል ግዙፍ የጋራ ወታራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ይህ ለተከታታይ 5ኛ ዓመት እንደሆነ ተነግሯል።
“ማሪን ሴክዩሪቱ ቤልት 2025” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የጋራ ልምምዱ በትናንትናው እለት በኢራን ክሀበር ወደብ አቅራቢያ ነው የተጀመረው።
- የሩሲያ እና የቻይና የጦር መርከቦች የሚሳይል ተኩስ ልምምድ አካሄዱ
- ሩሲያ በፓሲፊክ ቀጣና አሜሪካን ለመመከት ከቻይና ጋር በመሆን ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ነው
ልምምዱ "በተሳታፊ ሀገራት የባህር ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።
ልምምዱ የባህር ላይ ኢላማዎችን መምታት፣ ጉዳትን መቆጣጠር እንዲሁም የፍለጋ እና የነብስ አድን ስራዎች ላይ ያተኮረ ነው እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ወታራዊ ልምምዱ የሶስቱ ሀገራት የባህር ኃይሎች በቀን እና በማታ ከትላልቅ ካሊበር የጦር መሳሪያ እስከ አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች የተኩስ ልምምድ እንደሚያደርጉም ተነግሯል።
በዚሁ ወቅትም የጠላት መርከቦችን እና ድሮኖችን ኢላማ አድርጎ መምታትን እንደሚለማመዱም ተነግሯል።
ከአዘርባጃን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኦማን፣ ካዛኪስታን፣ ፓኪስታን፣ ኳታር፣ ኢራቅ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ስሪላንካ የተውጣጡ የባህር ኃይል ቡድኖች ልምምዱን እየተከታተሉ መሆኑም ታውቋል።