የ2015 የኒዩክለር ስምምነቱን እንደሚመልሱ ተመራጩ የኢራን ፕሬዚዳንት ገለጹ
ኢብራሂም ራይዚ በሀይማኖታዊው መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒ ጸድቆላቸው 8ኛው የኢራን ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተረጋግጧል
ፕሬዚዳንቱ በአሜሪካ ተጣሉትን ማዕቀቦች እንዲነሱ ጥረት እንደሚያደርጉና የተከፉ ኢራናውያንን እንደሚክሱ ይፋ አድርገዋል
ኢራን አሜሪካ እና ከአምስት የአውሮፓ ሀገራት ጋር ያደረገችውን የ 2015 የኒዩክለር ስምምነት ለመመለስ እንደሚሰሩ ተመራጩ የኢራን ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይዚ ዛሬ ፤ በሀይማኖታዊው መሪ አያቶላህ አሊ ሆሚኒ ጸድቆላቸው ስምንተኛው የኢራን ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተረጋግጧል።
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ጊዜ እንዳሉትም በአሜሪካ ተጣሉትን ማዕቀቦች እንዲነሱ ጥረት እንደሚያደርጉና የተከፉ ኢራናውያንን እንደሚክሱ ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ ማዕቀቡ እንዲነሳ ጥረት እንደሚደርጉ ይግለጹ እንጅ ከምዕራባውያን ጋር ግን ወደፊት ጠንካራ ትስስር እንዲኖር እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።
በአውሮፓውያኑ 2015 የተፈረመውና በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን የተደረገው የኒዩክለር ስምምነት ተመልሶ እንዲሰራ ጥረት አንደሚደርጉም ገልጸዋል።
ሰኔ 18 በኢራን በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ የሆኑት አዲሱ ፕሬዚዳንት በአሜሪካ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸው ይሁን እንጅ በኢራን ኢኮኖሚ ግን እንደማትደራደር አስታውቀዋል።
ቴህራን አሁን ላይ የበጀት ጉድለትን መሙላት፤ የካፒታል ገበያ ማረጋጋት፤ የዋጋ ንረትን ማረጋጋት፤ ኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲሁም የውኃ እና የኤሌክትሪክ እጥረትን ማስተካከል ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት ሁሉም ኢራናውያን ማለትም ምሁራን፤ ባለስጣናት፤ የኢራን ወዳጆች እና ሌሎችም በሀገሪቱ አዲስ ለውጥ እንዲመጣ ሊተባበሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።