አዲሱ ኢራን ፕሬዚዳንት ለእስራኤልም ሆነ ለምእራባውያን ትልቅ ስጋት ነው- እስራኤል
ኢብራሂም ሬሲ በኢራን በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 62 በመቶ ድመጽ በማግኘት ተቀናቃኞቻቸውን አሸንፈዋል
አዲሱ ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ ከተጣለባቸው ኢራናውያን አንዱ ናቸው
ኢብራሂም ሬሲ የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ለእስራኤልም ሆነ ለምእራባውያን ትልቅ ስጋት መሆኑን እስራኤል ገለጻች።
እስራኤል የኢራን ወግ አጥባቂው ክንፍ መሪው ኢብራሂም ሬሲ የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ የመጀመርያ አስታየቷን ሰንዝራለች።
“አዲሱ የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬሲ ለእስራኤልም ሆነ ለምእራባውያን ትልቅ ስጋት ናቸው”ም ብላለች።
“የሬሲ መመረጥ በኢራን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት አያቶላህ ዓሊ ካሜኒ መወሰናቸውንና ይህም ለምዕራባውያን እና ለእስራኤል ተግዳሮት መሆኑ የማይካድ ማስረጃ ነው” በማለት የከነስቲ ምክር ቤት የፀጥታና የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኃላፊ ራም ቤን ባርክ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩም የእስራኤል ጦር ሬዲዮ ዘግቧል።
የኢራን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱራህማን ፋዝሊ ወግ አጥባቂው እጩ ኢብራሂም ሬሲ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 62 በመቶ ድመጽ በማግኘት የኢራን ፕሬዝዳነት ሆነው በይፋ መመረጣቸው አስታውቀዋል።
ኢብራሂም በሙያቸው ዳኛ እንደነበሩ ይታወቃል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት አሜሪካ በሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ ከተጣለችባቸው ኢራናዊያን መካከል አንዱ ናቸው።
ኢራን ከእስራኤልም ሆነ ከምዕራቡ ዓለም ባላት ልዩነት እና ከሀገራቱ ጋር በየወቅቱ በምታደርገው ፍጥጫ የምትታወቅ ሀገር መሆኗ ይታወቃል።