በኢራን ፕሬዘዳታዊ ምርጫ አራት እጩዎች እየተወዳደሩ ነው
ለአስራ ሦስተኛው ጊዜ እየተካሄደ ባለው የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አራት እጩዎች እየተወዳደሩ ተገልጿል፡፡ በዚህ ውስጥ ሦስቱ ከአክራሪ ክንፍ ሲሆኑ አንድ እጩ ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ የሚራምድ የለውጥ አራማጆች የሚደገፍ ነው፡፡
የኢራን የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ካለው የመራጮች ተሳትፎ ማነስ ምክንያት የተነሳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በመጀመርያ ዙር የምርጫ ሂደት እንደማያልቅና ወደ ሁለተኛው ዙር እንደሚሄድ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡
በዚህ ምርጫ ሶስቱን አክራሪ ክንፍ ሚወክሉት ኢብራሂም ረኢሲ፣ ሙህሲን ሪዳኢ እና አሚር ሂሴን ሲሆኑ አብዱልናስር ደግሞ ለዘብተኛና የመካከል ፖለቲካ ክንፉን እንደሚወክሉም ታውቀዋል፡፡
በምርጫ ህጉ መሠረት የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የሚሆነውና መንበረ ስለጣኑን የሚቆናጠተው ሙሉ ድምጽ ያገኘ ተመራጭ ሲሆን እጩዎቹ በመጀመሪያው ዙር የሚጠበቅባቸውን ድምፅ ካላገኙ ግን ብዙ ድመፅ ያገኙ እጩዎች በሁለተኛው ዙር የሚወዳደሩ ይሆናል::
በፈረንጆቹ ከነሀሴ 2013 ጀምሮ ኢራን በፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ እየተመራች ያለች ሀገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡